(ዋዜማ ራዲዮ)- በርካታ የምስራቅ አፍሪቃ ሀገሮች የሳዑዲ ዐረቢያ ወዳጅ እየሆኑ ነው። የየመንን ቀውስ ተከትሎ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ኤርትራና ጅቡቲ ከሳዑዲ ጎን ተሰልፈዋል። ይህም የሱኒ እስልምና ዕምብርት የሆነችው ሳዑዲ በምስራቅ አፍሪቃ ከመቼውም ጊዜ የላቀ ተፅዕኖ የመፍጠር ዕድል ከፍቶላታል። ወትሮም ቢሆን ሳዑዲን በአይነ ቁራኛ ለምትመለከተው ኢትዮዽያ ጉዳዩ ራስ ምታት ይዞ መምጣቱ አልቀረም። የመሳካቱን ነገር እንጃ እንጂ ኢትዮጵያ ፊቷን ወደ እስራኤል ለማዞር ዳር ዳር እያለች ነው።አርጋው አሽኔ ዝርዝር አለው። አድምጡት