በኤርትራ ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኋላ ሊኖር ስለሚችለው የፖለቲካ ሁኔታ መናገር ለአብዛኞቹ ኤርትራውያንም ሆነ ለውጪ ታዛቢ ቀላል ጉዳይ አይደለም። ፕሬዝዳንቱ 70ኛ የልደት በዓላቸውን ለማክበር እየተሰናዱ ነው። የጤንነታቸው ሁኔታ በሀኪም እጅ ያለ ነው። ያለፉትን በርካታ አመታት በውጪ ሀገር እየተመላለሱ ህክምና አድርገዋል። እንዳውም አንድ ጊዜ ከሞት አፋፍ ነበር የተመለሱት።
ዛሬ ወይም ነገ ኤርትራን ያለ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ማሰብ በእርግጥ ትልቅ ፈተና ነው። ይህ ያሳሰባቸው የሚመስሉት ፕሬዝዳንቱ ባለፉት አመታት በአደጋ ጊዜ ሀገሪቱን በጋራ የሚመራ ኮሚቴ አዋቅረዋል። በዋነኝነት ወታደሩን ክፍል ያቀፈው ይህ ኮሚቴ ሀገሪቱን በአምስት ዞን በመክፈል እያስተዳደረ ይገኛል። ይህም ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ በኋላ የሚከተለው ወታደራዊ አስተዳደር ይሆናል የሚል ሰፊ ግምት እንዲኖር ሰበብ ሆኗል። ያለ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ለመለዮ ለባሹ ስምምነት ፈጥሮ ሀገር መምራቱ እንዲህ ቀላል ይሆን? ኢትዮዽያስ ምን እየዶለተች ይሆን?
(አርጋው አሽኔ ያዘጋጀው ዘገባን ከታች ያድምጡ)