- የኤርትራ የሳዑዲን ፀረ-ሁቲ ወታደራዊ ጥምረት ለመደገፍ ዳር ዳር ማለት ኢትዮዽያንና ጅቡቲን አስደንግጧል።
የየመን ቀውስ በአፍሪቃ ቀንድ ሀገሮች ዙሪያ እንደተፈራውና እንደተጠበቀው መፋጠጥ አስከትሏል። ኤርትራ በሳዑዲ ከሚመራው ጥምር ሀይል ጎን ለመሰለፍ መንታ መንገድ ላይ ናት። የኤርትራ እርምጃ ያስደነበራቸው የኢትዮዽያና የጅቡቲ መሪዎች ሳምንቱን ያሳለፉት ሳዑዲ መዲና ሪያድ ነበር።
ጠሚር ሀይለማርያም ደሳለኝና የጅቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማዔል ኦማር ጎሌህ በዚህ ሳምንት በተናጠል ወደ ሳዑዲ አረቢያ አምርተው ከሳዑዲ ባለስልጣናት ጋር ውይይት አድርገዋል። የሁለቱ መሪዎች ጉብኝት መገጣጠም አጋጣሚ አልነበረም። የኤርትራ በየመን የተሰማራው ሳዑዲ መር ጦር ደጋፊ መሆንና በቀይ ባህር የሚታየው አዲስ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ለኤርትራ መልካም አጋጣሚ ሲፈጥር ለኢትዮዽያና ጅቡቲ ግን አዲስ አደጋ የሚጋብዝ ሆኗል።
አርጋው አሽኔ ዝርዝር ዘገባ አለው-አድምጡት