የመንግስታቱ ድርጅት አጣሪ ኮምሽን በኤርትራ ላለፉት ሀያ አምስት አመታት ለተፈፀመው የሰብዓዊ መብት ረገጣ የሀገሪቱ መሪዎች በዓለም ዓቀፍ ፍርድ ቤት ጉዳያቸው ሊታይ ይገባል ሲል ምክረ ሀሳብ አቅርቧል። ኤርትራ ሪፖርቱን በጥብቃ አውግዛ የተቃውሞ ፊርማ በማሰባሰብ ላይ ናት።
ኤርትራ ከምዕራባውያን ጋር ያላት ግንኙነት ከመሻከሩ ባሻገር በሀገሪቱ ያለው ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ገፋፍቷቸው በገፍ እየተሰደዱ ያሉት ዜጎቿ ጉዳይ የአውሮፓ ህብረትንም እንቅልፍ የነሳ ጉዳይ ሆኗል። የአውሮፓ ህብረት የኤርትራ መንግስት ባህሪውን እንዲቀይር አልያም ራሱ እንዲቀየር ፍላጎት ማሳየት መጀመሩን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ይገልፃሉ። በአስመራ የአሜሪካ ኤምባሲ ሰራተኞች ለእስር መዳረግ በአስመራ ላይ ጥርስ አስነክሶባታል የሚሉም አሉ። ኢትዮጵያም በኤርትራ አንገት ላይ ሸምቀቆውን ለማጥበቅ እጇ እንዳለበት የአደባባይ ምስጢር ነው።
የኤርትራ ጉዳይ በቀጣይ በፀጥታው ምክርቤት የሚወሰን ይሆናል። የፀጥታው ምክርቤት የኤርትራ ባልስልጣናት ጉዳይ “በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ይታይ” ብሎ ከወስነ ጉዳዩ ለኤርትራ መሪዎች ከእስከዛሬው ሁሉ የከፋና መዘዙም ቀላል አይደለም። ኤርትራን በፀጥታው ምክር ቤት ፊት ማን ይታደጋታል? አርጋው አሽኔ ዝርዝር ዘገባ አለው-እነሆ ያድምጡት