አሁን ባለው የኢትዮዽያ አስተዳደር ውስጥ “መብቴ አልተከበረም” የሚል ብሄር ወይም ጎሳ እገነጠላለሁ ቢል ምንድነው ወንጀሉ? መገንጠልስ መብት አይደለም ወይ? ኢትዮዽያዊ ብሄረትኝነት በአዲስ ማንነት ከተተካ ቆየ፣ ስለምን እናንተ “በሞተና ባከተመ ጉዳይ” ላይ መወያየት መረጣችሁ? በእርግጥ ኢትዮዽያዊ ማንነት ያከተመ ጉዳይ ነውን? በሀገሪቱ በቁጥር ትልልቅ ብሄረሰቦች እንዳሉ ሁሉ ትናንሾችም አሉ ታዲያ ራስን የማስተዳደር ጥያቄ ሲያነሱ በእኩል ይስተናገዳሉ? የክልልነት የወረዳነት ወይም የመገንጠል ጥያቄ ቢያቀርቡ የሚስተናገዱት እንዴት ነው? ከናንት ከአድማጮቻችን የደረሱንን ጥያቄዎች መነሻ አድርገን ውይይታችንን እንቀጥላለን። ዋዜማን አድምጡ፣ አጋሩ