ዋዜማ ራዲዮ- የአፍሪካ ቀንድ ፖለቲካን ለሚከታተል ሁሉ አንድ የአሜሪካ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን ከሰሞኑ ወደ አስመራ በምስጢር መጓዛቸው አስገራሚ ይመስላል። አስመራና ዋሽንግተን ምን እያደረጉ ነው? በክፍለ ቀጠናው እየሆነ ያለው ኤርትራ ለመሸጉ የኢትዮጵያ አማፅያንና በስልጣን ላይ ላለው መንግስት ምን ይዞ ሊመጣ ይችላል?
የተሰናበትነው ሳምንት ለሁለቱ የምስራቅ አፍሪቃ ባላንጣ ሀገሮች ከፍያለ የዲፕሎማሲ ትዕይንት የታየበት ነበር። ኢትዮጵያ በፀጥታው ምክር ቤት የተለዋጭ አባልነት መቀመጫ በከፍተኛ ድምፅ አግኝታለች። ኤርትራ በበኩሏ መሪዎቿን በአለም አቀፍ ፍርድ ቤት እንዲቆሙ የሚጠይቀውን ምክረ ሀሳብ(Resolution) በመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብት ካውንስል ለዘብ እንዲል ሆኗል፣ ምንም እንኳ ክሱና ዲፕሎማሲያዊ ፈተናው ከመሰረቱ ባይቀየርም። ይህንና አጠቃላይ ሰሞነኛ ጉዳዮችን ተመልክተናል። የሚከተለው የአርጋው አሽኔ ዘገባ የሚያጋራችሁ ይኖረዋል። አድምጡት