ዋዜማ -በደቡብ ክልል ስር የሚገኙ 6 ወረዳዎች በኢትዮጵያ አስራ ሁለተኛ ክልል ለመሆን ላቀረቡት ጥያቄ ህዝበ ውሳኔ ያደርጋሉ፡፡ ይህን ለማስፈፀምም 541 ሚሊየን ብር ያስፈልገኛል ሲል የኢትዮጰያ ምርጫ ቦርድ መንግስትን ጠይቋል፡፡ መንግስት ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በበጀት ጥያቄው ላይ ምላሽ አልሰጠም።
ምርጫ ቦርድ ህዝበ ውሳኔውን እስከ ጥር ወር ድረስ ለማካሄድ የሚያስችለው ዝግጅት ቢያደርግም ከክልሎች በኩል የሚፈልጋቸው መረጃዎች በቶሎ ሊደርሱት አልቻሉም።
ህዝበ ውሳኔ በሚደረግባቸው አንዳንድ አካባቢዎች አሁንም የፀጥታ ችግር መኖሩን ዋዜማ በየጊዜው ካሰባሰባቸው መረጃ እናውቃለን። በህዝበ ውሳኔው ሂደት እና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ዋዜማ የምርጫ ቦርድ ሊቀመንበር ብርቱካን ሚደቅሳን ጠይቃለች ። የቃለ ምልልሱን ጨመቅ ከታች በድምፅ ያድምጡት