በኢትዮጵያ የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መለዮ ለባሹ በዕለት ተዕለት የአስተዳደር ስራ ውስጥ እጁን እንዲያስገባ በር ከፋች ዕድል ነው። ከአስቸኳይ ጊዜው በኋላ የወታደሩ ክፍል ስነ ልቦናና ተሞክሮ ሀገሪቱን ወዴት ይመራታል? በእርግጥ መለዮ ለባሹ ለስልጣን ባዳና ባይተዋር አይደለም። ሀገር መርቶና የሲቪል አስተዳደሩን ገሸሽ አድርጎ ሲንቀሳቀስ ግን ያሁኑ ከሃያ አምስት አመታት ወዲህ እንግዳ ነው። አስቲ ውይይታችንን አድምጡ አጋሩ ሀሳባችሁን ስደዱልን
ክፍል አንድ ውይይት በዶ/ር ደረሰ ጌታቸው ፣መስፍን ነጋሽ እና አርጋው አሽኔ