Saudi vessels are seen at Assab in Eritrea on 15 November 2017
Saudi vessels are seen at Assab in Eritrea on 15 November 2017

ዋዜማ ራዲዮ- ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በክፍለ ቀጠናው ራሷን የአካባቢው ሀያል ሀገር ለማድረግ እየተቀሳቀሰች ያለችው ሳዑዲ አረቢያ ባለፈው ሳምንት ሶስት የጦር መርከቦቿን በኤርትራ አሰብ ወደብ ማስፈሯን ለዋዜማ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ተናገሩ።
የሳተላይት መረጃን ዋቢ ያደረጉት እነዚህ ምንጮች ሳዑዲ በአሰብ ወደብ ጦር መርከብ ስታሰፍር ያሁኑ የመጀመሪዋ ነው። የጦር መርከቦቹ ለረጅም ጊዜ በአሰብ የመቆየት ዕቅድ ይኑራቸው አይኑራቸው የታወቀ ነገር የለም።
ከዚህ ቀደም የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ቢያንስ ስድስት የጦር ጀልባዎችንና የአውሮፕላን መንደርደሪያ መርከቦችን በአሰብ ማስፈሯ ይታወሳል።
ሳዑዲ ባላት ከፍተኛ የመስፋፋት ፍላጎትና ከኢራን ጋር በገባችበት ፉክክር ሳቢያ ወታደራዊ ሀይሏን በከፍተኛ መጠን እያሳደገች መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ።
በየመን እያደረገች ላለው ጦርነትም በኤርትራ አሰብ ወደብ ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ጋር በጋራ የአሰብን ወደብ በኪራይ በመውስድ የጦር ሰፈር መገንባቷ ይታወቃል።
ሌላው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የጦር ሰፈር ግንባታ በሶማሊላንድ ግማሽ በግማሽ የተከናወነ ሲሆን በዚህ አመት መጨረሻ ስራ እንደሚጀምር ይጠበቃል። ቱርክ በተመሳሳይ በሶማሊያ የጦር ሰፈር ግንባታ ላይ ስትሆን ቢያንስ ስድስት ሀገሮች በጅቡቲ የጦር ሰፈር አላቸው። ዝርዝር የድምፅ ዘገባውን ያድምጡት

https://youtu.be/MCh8cjsiPaw