ዋዜማ ራዲዮ-በሰላማዊ መንገድ በሀገር ቤት እንታገላለን ብለው የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከመኖራቸው ያለመኖራቸው ይበጃል በሚል የሚከራከሩ አሉ። የለም የሀገር ቤት የፖለቲካ ፓርቲዎች ወሳኝ ሚና አላቸው፣ አሁን በራሳቸው ውስጣዊና ገዥው ፓርቲ በደነቀረው ፈተና ተተብትበው ነው በሚል የሚሟገቱላቸውም አልጠፉም። የሰማያዊና የመኢአድ መሪዎች ከገጠሙን ተደራራቢ ፈተናዎች ባሻገር ትግሉን አንድ እርምጃ ለማራመድ ያደረግነው ጥረት ስምሮ አሁን በስልጣን ላይ ያለው መንግስት በህዝብ የተጠላና ተዓማኒነት ያጣ ሆኗል ብለዋል። መሪዎቹ በአሜሪካ የገቢ ማሰባሰቢያ ለማድረግና የድርጅቶቻቸውን ትግል ለማጠናከር እቅድ አላቸው። በመጪው የአዲስ አበባና ድሬዳዋ የአካባቢ ምርጫ በጥምረት ለመሳተፍም አቅደዋል። ከገዥው ፓርቲ ጋር በሚደረገው ድርድር ስማያዊ ራሱን ሲያገል መኢአድ በድርድሩ ቀጥሏል። ሁለቱ ፓርቲዎች ለመዋሀድም ሀሳብ አላቸው። ተከታዩ ዘገባ ዝርዝር አለው።
https://youtu.be/saB-OwBuok8