Dr Negeri Lencho
Dr Negeri Lencho

ዋዜማ ራዲዮ- ባለፉት ቀናት ከኮምኒኬሽን ጉዳዮች ሚንስትርነት ሀላፊነታቸው መነሳታቸው በስፋት ሲነገር ቢቆይም ሚንስትሩ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ አሁንም በስራ ገበታቸው ላይ መሆናቸውን አዲስ አበባ የሚገኙ ሪፖርተሮቻችን አረጋግጠዋል።
በዛሬው እለት ሚንስትሩ እንግዳ ሲቀበሉና ሲያነጋግሩ የነበረ ሲሆን ከስልጣን የመልቀቃቸውን አልያም የመነሳታቸውን ጉዳይ አንስተው ለጠየቋቸው የቅርብ ወዳጆቻቸው ነገሩ ሀሰት ነው፣ ይህን የሚሉትም የተለየ አጀንዳ ያላቸው አካላት ናቸው ሲሉ ተደምጠዋል።
ከወትሮው የተለየ ትህትና የሚነበብባቸው ዶ/ር ነገሪ ስኞ ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ ለመንግስታዊው የቴሌቭዥን ድርጅት በወቅታዊ ጉዳዩች ላይ ሰጥተዋል።
መግለጫው ሚንስትሩ ከስራ ተነስተዋል መባሉን ለማስተባበልና በስራ ላይ እንዳሉ ለማሳየት ያለመ ሳይሆን እንዳልቀረ ግምታቸውን የነገሩን አሉ። ዶ/ር ነገሪ የኦህዴድ አባል ሲሆኑ በመምህርነት ላለፉት አመታት አገልግለዋል።ስለ ሚንስትሩ ተጨማሪ ማንበብ ከፈለጉ- LINK https://goo.gl/3Kgx1V