ዋዜማ ራዲዮ- ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ፣ ትልቅ ትኩረት ከሳቡት ጉዳዮች አንዱ የኢኮኖሚው ዘርፍ ነው፡፡ እናም የዐቢይ መንግሥት በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ዘርፍ ምን ለውጦችን እንዳደረገ፣ የኢኮኖሚ አያያዙ ምን እንደሚመስል እና ኢኮኖሚው ላይ የተጋረጡት ችግሮች ምን እንደሆኑ ለማወቅ፣ ዋዜማ ሬዲዮ አዲስ አበባ የሚገኙ አንድ ገለልተኛ የምጣኔ ሃብት አማካሪ ቀጥራ የዳሰሳ ሪፖርት እንዲዘጋጅላት አድርጋለች፡፡

“የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በዐቢይ አህመድ እጅ- ተስፋ ያለው ምሪት ወይስ ላም አለኝ በሰማይ?” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ይኼው የዳሰሳ ጥናት፣ በመንግሥት ያንድ ዐመት የኢኮኖሚ ማሻሻያ አፈጻጸም ላይ ያተኮረ የሙያተኛ ግምገማ ተደርጎ ሊወሰድ የሚችል ነው፡፡

የኢትዮጵያ ገዥዎች፣ ከአጼ ኃይለ ሥላሴ እስከ ኮሎኔል መንግሥቱ፣ ከመለስ ዜናዊ እስከ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ እና ዐቢይ አሕመድ ድረስ “የመሪዎቹ እሳቤ፣ ሕልም እና ምኞት በሀገሪቱ የኢኮኖሚ አመራራቸው ውስጥ በጉልህ መንጸባረቁ አንዱ የጋራ መለያ ባሕሪያቸው ነው” የሚለው የግምገማ ሪፖርቱ ማሰሪያ ሆኖ ቀርቧል፡፡ የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የኢኮኖሚ አመራርም፣ ከራሳቸው ግላዊ እሳቤ እና ምኞት የሚመነጭ ብዙ ተስፋዎች ግን ደሞ ትንሽ ተግባራት የሚታይበት እና ትላልቅ ስጋቶች የሚያንዣብቡበት እንደሆነ የተለያዩ አብነቶችን በማጣቀስ ያብራራል፡፡ ሙሉ ሪፖርቱን ለማግኘት እዚህ ይጫኑ