[facebookpost url=””]

One of Addis Ababa Iconic Monument in front of National Theater
One of Addis Ababa Iconic Monument in front of National Theater
  • ከተሜ የፖለቲካ ለውጥ (የዴሞክራሲ)የስበት ማዕከል ነውን? መልሱ ያከራክራል።  ለምን ቢባል- መሬት ላራሹን አንግበው ከተነሱት ተማሪዎች አንዳንዶቹ ከገጠር የተገኙ ናቸው። የባላባት ልጆች አልነበሩም እንዴ አብዮቱን ከፊት ሆነው የመሩት? አስቲ መልሱን በጋራ እንፈልግ።

የከተሞች እና የመከተም (urbanization) ነገር በአገራችን ማኅበረሰባዊ፣ ባህላዊና ፖለቲካዊ ሕይወት ውስጥ ያላቸው ቦታ ዘመን በገፋ መጠን በእጅጉ እየጨመረ መምጣቱ ቢታወቅም በምርምርም ሆነ በሕዝብ አደባባይ ብዙም አልተባለለትም። ነገሩን ከከተሞች ታሪክ፣ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ፣ ባህላዊ ገጽታ እንዲሁም ፖለቲካዊ ስፍራ አንጻር መመልከት ይቻላል:: በዚህ ዝግጅታችን ስለከተሞች ምንነት፣የኢትዮጵያ ከተሞች በየዘመኑ ከነበሩ መንግሥታት እና ፖለቲካዊ ድባብ ጋራ የነበራቸውን ግንኙነት እናወሳለን። የከተሞች መፈጠርን ግድ የሚለው ነገር ምንድን ነው? ከተማና ገጠር ሲባል በተለምዶ የሚሳለው ምስል እንደምን ያለ ነው፣ ትክክልስ ነው? ከተሞቻችን እና መንግሥቶቻችንስ እንደምን ባጁ? እያለ ውይይቱ ይቀጥላል። የውይይቱ ተካፋዮች ሽመልስ ቦንሳ (ዶ/ር) እና ደረሰ ጌታቸው (ዶ/ር) በየትምህርት ዘርፎቻቸው ስለከተሞች አጥንተዋል፣ ያስተምራሉም። ውይይቱን ትወዱታላችሁ፣ ቢያንስ አንድ ሐሳብ ስለሚያጭርባችሁ።
እነሆ ግብዣችን!  ዋዜማን ለወዳጆችዎ መጋበዝን አይዘንጉ