Addis Ababa City Hall
Addis Ababa City Hall

በኦሮሚያ የተከሰተውን ህዝባዊ አመፅ ተከትሎ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ይገቡኛል የሚላቸውን ጥቅሞች የሚያጠና ግብረሀይል አቋቁሟል። ህገመንግስቱ ዕውቅና የሚሰጠው በብሔር ለተደራጁት ክልሎች ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ለመሆኑ አዲስ አበባ ከሌሎች ክልሎች እኩል የመዳኘት መብት አላትን? በሀገሪቱ መሰረታዊ የፖለቲካ ለውጥ ካልመጣ “የኦሮሚያ ልዩ መብት ብቻውን የኦሮሞን መሰረታዊ ጥያቄ አይመልስም” ይላል አንዱ ተወያይ። ሌላው እንግዳችን “የኦሮሞ ህዝብ የብሄር እኩልነት መብቱ ካልተረጋገጠ የስርዓት ለውጡ ብቻውን ዋስትና የሚሰጠው አይሆንም” ሲል ያስረዳል። እስቲ ውይይቱን አድምጡት –እነሆ ከታች ሌላ አስተያየትም አለ ማድመጥ አይዘንጉ

ተጨማሪ ውይይት ከታች ይመልከቱ

ትኩረት መደረግ ያለበት የስርዓት ለውጥ ማምጣት ላይ መሆን አለበት

Semahagn Gashu (PhD)
Semahagn Gashu (PhD)

ህገ መንግስቱ የኦሮሞን ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችል ቁመና የለውም ስለዚህ በሀገሪቱ መሰረታዊ የፖለቲካ ለውጥ ካልመጣ የኦሮሚያ ልዩ መብት በአዲስ አበባ ብቻውን የኦሮሞን መሰረታዊ ጥያቄ አይመልስም ፣ ስለዚህም ትኩረት መደረግ ያለበት የስርዓት ለውጥ ማምጣት ላይ መሆን አለበት። ኢህአዴግ እያንዳንዱን የኦሮሞ ጥያቄ ለስልጣኑ ማራዘሚያ በሚያመቸው መልክ እየሸረበ መቆየት እንጂ ችግር የመፍታት ፍላጎትና ብቃት የለውም። ዶር ሰማኸኝ ጋሹ የሚሰጠውን አስተያየት እነሆ ከታች ሌላ አስተያየትም አለ ማድመጥ አይዘንጉ

 

አዲስ አበባ ከሌሎች ክልሎች እኩል ሉዓላዊ ናት?

Dr. Tsegaye Ararsa
Dr. Tsegaye Ararsa

አዲስ አበባ የኦሮሚያ ተፈጥሯዊ ይዞታ ስትሆን ፌደራል መንግስቱ ደግሞ እንግዳ ነው። የአስተናጋጇን የኦሮሚያን ባህል ቋንቋ አክብሮ መኖር ይጠበቅበታል። የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ራሳቸውን በብሄር ለመግለፅ የሚቸገሩ ስለሆነ ከተማይቱ የነሱን የመኖር መብት ባረጋገጠ መልኩ ትተዳደራለች። ዶር ፀጋዬ አራርሳ ተጨማሪ ማብራሪያ አለው