[በነገራችን ላይ]

ዋዜማ ራዲዮ- በሰማንያ ዓመቱ በሞት ያጣነው ሰለሞን ዴሬሳ ቀርበው ሲመለከቱት ይበልጥ ጥያቄ የሚያጭር ማንነት ያለው፣ በዘመናዊው የኢትዮጵያ ስነ ፅሁፍ ውስጥ አማፂ ሊባል የሚችል ማንነት ያለው፣ ሙግትና ተጠየቅን የሚወድ ነበር። መስፍን ነጋሽ ከሱራፌል ወንድሙ ጋር የሚያውቁትንና የተረዱትን የሰለሞን ማንነትና ስራዎቹን አንስተው ይወያያሉ። አድምጧቸው።

መስፍን ነጋሽና ሱራፌል ወንድሙ ያደረጉትን ቆይታ ለመስማት የድምፅ ማህደሩን  እዚህ ይጫኑ

ሰለ ሰለሞን

“የአዲስ አበባ ልጅ ነኝ፡፡ ሰፈር የለኝም፡፡ ያደኩት ስድስት ኪሎ፣ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ሆሰፒታል ጓሮ ቀጥሎም ትምህርት ሚኒስቴር አሁን ህንፃው የቆመበት መንደር አራት ኪሎ፤ የአራት ኪሎ ልጅ ነኝ” ይላል ሰለሞን ዴሬሳ፡፡
ጩታ የምትባል መንደር ወለጋ ውስጥ ከግንቢ 45 ደቂቃ የምታሰኬድ መንደር ውስጥ ነው የተወለደው ሰለሞን። እስከ አራት አመቱ እድገቱ እዛው ጩታ ውስጥ ነው፡፡
ፒያሳ፣ ኃብተጊዮርጊስ አካባቢ፣ መርካቶም፣ ልዕልት ዘነበወርቅ ት/ቤት አካባቢ አድጓል፤ ከዛም ማዛንቺስ፣ጉለሌ ስድስት ኪሎ ትምህርቱን ተከታትሏል፡፡ መድኃኒዓለም ትምህርት ቤት ተምሯል በጉለሌ።
“አዲስ አበባ ያላደኩበት ሰፈር የለም” ይላል ሰለሞን ዴሬሳ፤ የበኩር ልጅ ነው ለእናቱ ። ትምህርት በህይወቱ እንዳያልፈው ወላጅ እናቱ ቁርጠኛ አቋም ነበራቸው። እርሳቸው ያለፋቸው ትምህርት የመማር ዕድል ለእርሱ እንዳያልፈው ለፍተዋል።
ልዕልት ዘነበወርቅ ት/ቤት አራት ዓመት ተኩል ሲሆነው ገባ። መደኃኒዓለም ትምህት ቤት፣ ተፈሪ መኮንን ትምህትቤት፣ እያፈራረቀ ትምህርቱን ቢከታተልም “አስር ዓመት እስኪሆነኝ ድርስ ፊደል መቁጠር አልቻለኩም” ነበር ይላል ሰለሞን።
ጀነራል ዊንጌት ት/ቤት የሁለተኛ ደረጃ ትምህቱን ሲያጠናቅቅ የአሰራ ስድስት ዓመት ጎረምሳ ነበር። አዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲ ኮሌጅ፣ከዚያም በፈረንሳይ ሃገር በዴቱሉዝ ዪኒቨርስቲ የህግ ትምህቱን ተከታሏል።
በፈረንሳይ በነበረው ቆይታ ከታዋቂው ኢትዮጲያዊ ሰዓሊ እስክንድር በጎሲያን ጋር የእድሜልክ ወዳጅ ሆነው የቀሩት በዚህ ትምህርት ቤት በነበራቸው ቆይታ አማካኝነት ነው።
በ1953 ዓ.ም ወደ አሜሪካን አገር የተጓዘው ሶሎሞን ዴሬሳ ለመጀመሪያ ጊዜ በሎስ አንጀለስ ከተማ ይኖር ነበር። በተባበሩት መንግስታት ድርጅትም የፈረንሳይኛ ቋንቋ ወደ እንግሊዘኛ የመተርጎም ስራ ሰርቷል በመጀመሪያ የአሜሪካን አገር ቆይታው።
ወደ ኢትዮጲያ በ1959 ተመለሰ። በአገር ቤት በነበረው ቆይታ በኢትዮጲያ ቴሌቭዥን እና ራዲዮ ድርጅት አገልገሏል፡፡ በጊዜው “አለም” የተሰኘ የህዝብ ግንኙነት ድርጅት ከጓደኞቹ ጋር በጋራ በመሆን አቋቁሞ የሰራ ነበር። በጊዜው አዲሰ ሪፖርተር በተሰኛ የእንግሊዘኛ መፅሔት ላይ በፀሐፊነት ስርቷል
“ልጅነት” የሚለው የበኩር መፀሐፉ ለህትመት የበቃው በ1963 ዓ.ም ነበር። በ1965 ዓ.ም አለም አቀፍ የፀሃፊያን ፕሮግም ላይ ለመሳተፍ አይዋ ዪኒቨርስቲ አሜሪካን አገር መጣ። በዚሁ አመት ልጁ ገላኔ ተወለደች።
ከልጁ ገላኔ መወለድ በኃላ ሶሎሞን ዴሬሳ በአሜሪካ አገር በሚኒሶታ ዪኒቨርስቲ የፊሎሶፊ ትምህርቱን ተምሮ በዪኒቨርሰቲው የኮምፓራቲቭ ሪሊጅን አሰተማሪ ሆኖ አገልግሏል።
“እኔ በህይወቴ ቢሮክራሲ የሚባል ነገር ተስማምቶኝ አያውቅም። ልክ ልጄ ኮሌጅ ስትጨርስ አኔም ከዪኒቨርስቲ ለቅቄ ወጣሁ።ከዩኒቨርሲቲ ቢሮክራሲ ተለያየሁ። እኔ ቢሮክራሲ የሚባል ነገር ተስማምቶኝ አያውቅም። ምንም አይነት። ከሞትኩ በኃላም መንግስተ ሰማያት የሚባል ቦታ እንዳለ እዚያ ቢሮክራሲ ካለ እነ የጴጥሮስን እነ ጳውሎስን ማሰፈቀድ፣ ማሰፈረም ካለ እንደማይሰማማኝ አውቃለሁ።” ብሏል ሶሎሞን ለኢትዮጲያ ቴሌቭዥን ቅዳሜ መዝናኛ በተስኘ ፕሮግም ላይ።
ደራሲ ስብሐት ገብረእግዚብሄር ደግሞ ሰለሶሎሞን እንዲህ ነበር ያለው “ሰው መስማት ይችልበታል እሱ፡፡ ለአብዛኛው ሰው ሰትነግር አየመጠንክ እየቀነስክ ነው የምታወራው። ከሶሎሞን ጋር ስትሆን፣ እንደኔ ከሆንክ ዝም ብልህ ነው የምታወራው። በቃ የመጣልህን ነው የምታወራው። መስማት ይችልበታል ማለት ነው”
በ1973 በሳይኮቴራፒ ላይ ልዪ ፍላጎት ያደረበት ሶሎሞን በገሰታልት ኢኒስቲትዩት ኦፍ ትዊን ሲቲስ የገሰታልት ቴራፒ ትምህርት ተከታትሏል። ቀጥሎም ባጋጠማቸው የህይወት ትግል ውስጥ ሰዎችን “መፍትሔ ፍለጋ” ያሰተምር ነበር።
ከዚያም በ1992 ዓ.ም “ዘበተ እልፊቱ ወለሎታት” የተሰኘውን መፀሐፉ አሳትሟል፡፡

የሰሎሞን ዴሬሳ ቃለ መጠይቆች

·       ከያሬድ ጥበቡ ጋር በዜጋ መፅሔት የታተመ ጥር 1995 PDF 

·       The Hyphenated Ethiopia, Addis Reporter PDF

·       ከጋዜጠኛ ደረጀ ኃይሌ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ

·       ከግርማ ደገፋው ጋር በኢቲቪ 120 ፕሮግራም

·       ኢቲቪ አዲስ መዝናኛ ፕሮግራም
የሶሎሞን የደራሲነት፣ የገጣሚነት፣ የጋዜጠኝነት፣ የተመራማሪነት፣ የወለልቶ ህይወት እንዴት ነበር? ሶሎሞን ዴሬሳ፣የማይዳሰስ ውብ ቅርፅ በሚል – መሰፍን ነጋሽ ህይወቱን በወፍ በረር ያሰቃኘናል፡፡ እንድታደምጡ ተጋብዛቹኃል።