muslim comዋዜማ ራዲዮ-በኢትዮጵያ የተቀጣጠለው የለውጥ እንቅስቃሴ ለውጤት እንዲበቃ ሁሉም ወገን ዘር ሀይማኖት ሳይገድበው በላቀ ሀላፊነት የድርሻውን እንዲወጣ የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ጥሪ አቀረበ።

ኮሚቴው ባደረሰን መግለጫው በሀገሪቱ የነገሰውን ኢ-ፍትሀዊነት መቀልበስ የሚቻለው ሁሉም ዜጋ የድርሻውን ሀላፊነት ሲወጣ ብቻ ነው።

“ይህ ህዝባዊ ተቃውሞ የዓመታት የተከማቸ የህዝብ ብሶት ውጤት እንጂ የአንድ ጀምበር ስሜታዊነት የወለደውክስተት አይደለም፡፡ አገሪቱንበመምራት ላይ ያለው መንግስት ለህዝብ ጥያቄ ዋጋ ያለመስጠትና የስልጣን ምንጭ የሆነውን ህዝብ የመናቅ ባህል ስር የሰደደ በመሆኑምክንያት ህገ-መንግስታዊና ሰብዓዊ መብቱን በሰላማዊ መንገድ የጠየቀን የህብረተሰብ ክፍል እንኳእንደ ጠላት ሲመለከትና በሽብርተኝነት ሲፈርጅ ቆይቷል” ይላል መግለጫው።

ዜጎችን እርስ በእርስ የሚያጋጩና የጥላቻ አስተያየቶች ሀገርን አደጋ ላይ የሚጥሉ በመሆናቸው ሁሉም ወገን ጥንቃቄ ማድረግ አለበት ብሏል ኮሚቴው።

[የመግለጫውን ሙሉ ይዘት እዚህ ይመልከቱ]Press-Release-by-Arbitration-Committee