የብሪታንያው የዜና አገልግሎት (BBC) የስርጭት አድማሱን የሚያሰፋበትን አዲስ ዕቅድ መንደፉን አሳውቁዋል። በማስፋፍያው እቅድ ላይ በሚዛናዊ የዜና ዘገባ ረገድ የዲሞክራሲ ችግር የሚታይባቸው ናቸው ያላቸውን ጥቂት የዓለም አገራት ለመድረስ የሚያስችሉ በልዩ ልዩ ቁዋንቁዋዎች የሚሰራጩ ፕሮግራሞች የማዘጋጀት ትልም አለው። BBC ስርጭርቱን ሊያስፋፋ ከሚፈልግባቸው የዲሞክራሲ ችግር የሚታይባቸው አገሮች መካከል ኢትዮጵያ አንዱዋ ናት።
ይህ ዜና ከተሰማ በሁዋላ ፕሮግራሙ ሲጀምር ኦሮምኛ ቁዋንቁዋን የስርጭቱ አካል እንዲያደርግ የሚጠይቅ የፌስቡክና የትዊተር ዘመቻ ተኪያሂዱዋል። እስካሁን ድረስ በቀጠለው በድረገጽ የድጋፍ ፊርማ የማሰባሰብ ዘመቻ ክ27 ሺህ በላይ የሚኾኑ ሰዎች የቢቢሲ እቅድ ኦሮምኛን እንዲጨምር በመጠየቅ አቤቱታቸውን አሰምተዋል። (የመዝገቡ ሀይሉን ዘገባ እዚህ ያድምጡ)
በአፍ መፍቻ ቁዋንቁዋነት ጥቅም ላይ በመዋል ከሌሎች የኢትዮጵያ ቁዋንቁዋዎች ሁሉ የበላይነት ያለው የኦሮምኛ ቁዋንቁዋ በጥቅም ላይ የሚውልባቸው የመገናኛ ብዙኃን ሙሉ በሙሉ በመንግስት ቁጥጥር ስር ያሉት ብቻ ናቸው። የኦሮሞን ሕዝብ ጉዳዮች በአማርኛ ቁዋንቁዋ ያቀርቡ የነበሩ ጥቂት የግል ጋዜጦች የነበሩበትም ዘመን የነጻ ሚዲያውን ጠራርጎ ባጠፋው የመንግስት ተጽዕኖ ምክንያት ታሪክ ከኾኑ ቆይተዋል። በመንግስት የሚሰራጩት የኦሮምኛ ቁዋንቁዋ ሚዲያዎች በሌሎች ቁዋንቁዋዎች እንደሚሰራጩት ሁሉ የመንግስት የፕሮፓጋንዳ መገልገያዎች ናቸው።
ገና ብዙ ሊሰራበት በሚገባው የኦሮምኛ ሚዲያ እጥረት ውስጥ ቢቢሲ በሚጀምረው ኢትዮጵያን ዒላማው በሚያደርግ ዕቅድ ውስጥ የኦሮምኛ ቁዋንቁዋ ፕሮግራም መካተቱ አስፈላጊነት አጠያያቂ አይደለም። ይህ በማኅበራዊ ሚዲያና በድረገጽ የተደረገው ዘመቻ የሚያመጣው ተጽዕኖ ምንም ይሁን ምን በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ተጨማሪ የመገናኛ ብዙኃን እንደሚያስፈልጋቸው ያሳየ ወሳኝ መልዕክት ማስተላለፉ በራሱ አንዱ የዘመቻው ስኬት ነው።
Thanks Mezgebu for this report! Betam enamesegenalen!!
Afan oromo the largest languege in ethiopia
That great report, thanks Mezgabu. You are doing your job well!
Thanks Mezgebu for your balanced and professional report. It is realy a great work.
Baga gamadan umatni oromo hundi.bbc afaan oromoo kanati sabni hunduu akka mallatesitan
Thanks for your support and feedback gaaltomii
You’re racist. Do you think all Ethiopian people speak Oromifa? Should regions other than Oromo have to be put aside in this very important matter? Don’t be selfish. Bunch of asshole. When will start thinking!? Ethiopian population is 90 million not 30 million.
you are the resist here, dude. why do you hate it when people speak Afaan Oromo? it is the language of the future. it is not going to be your precious only Amargna anymore.
Thank you very much for your report
As every body know the fact that Oromo peoples take half of the Ethiopian regime ( nearly about 50 million people). Even though the population is high this people have no voice in the world, mean that this people is voiceless! It has been so long long time that this people is killed, murdered, harassed by the regime starting from the old era ( about more than two centuries as a history state it). There for we concluded that, this regime (which is called as EPRDF) should be resigned and must be decline. Otherwise, We Oromo people (especially students and farmers) continue our struggle for democracy.
afan oromoo is the most african launguage spoken
አማራጭ ሚዲያ በጠፍበት ሀገር ላይ የቢቢስ ሀሳብ እንደ ጥሩ ጎኑ የማየው ነው በተለይ በኛው ሀገር መግባቢያ መሆኑ ይበልጥ አስደስቶኛል እናንተም ጥሩ ስራ እየሰራችሁ ነው በርቱ ቀጥሉበት
One of the problems of oromo people in Ethiopia is that there is no independent media which serves the people. So, it will be great news if BBC starts it’s distribution with Affaan Oromo
I believe this is the most balanced report that Wazema has done since it began broadcasting. If you guys report in this balanced way, I’m sure you’ll even attract people who may listen to you with skepticism. Balanced and positive, that what we need in the Ethiopian media landscape, especially when it comes to talking politics.
የሀገሬ ቋንቋ በአለም ደረጃ እንዲደመጥ የሚደረገው እንቅስቃሴ ደስ ቢለኝም በኦሮምኛ ቋንቋ ስርጭት እጀምራለው የሚለው ቢቢሲ ግን የኢሉሚናንቲዎች አባል በመሆኑ ከዚህ ጀርባ የሆነ መጥፎ ነገር እንዳለ ይሰማኛል ብቻ ሀገራችን ኢትዮጵያ ሰላም ያርግልን