ዋዜማ ራዲዮ- የአርበኞች ግንቦት ሰባት ከፍተኛ አመራር የሆኑትና በአደባባይ ምሁርነታቸው የሚታወቁት ዶ/ር ታደስ ብሩ ኬርሰሞ በሚኖሩበት ሀገር እንግሊዝ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ስጥተው በዋስ ተለቀዋል። ጉዳያቸው ከአንድ ሳምንት በኋላ እንደገና ይታያል። ዶ/ር ታደሰ ከሚመሩት ድርጅት አርበኞች ግንቦት ሰባት ጋር በተያያዘ ወደ ኤርትራ ያደረጉት ጉዞ የአሸባሪዎችን ካምፕ በመጎብኘት በሚል አስወንጅሏቸዋል። እንግሊዝም ሆነች ሌሎች ምዕራባውያን አርበኞች ግንቦት ሰባትን አሸባሪ ብለው አልፈረጁም። ታዲያ ውንጀላው እንዴት ፍርድ ቤት ደረሰ አርጋው አሽኔ በተመሳሳይ ድንግዝግዝ የህግ ማጣቀሻ በምዕራቡ አለም የደህንነትና የፀጥታ ተቋማት በቁጥጥር ስር ለመዋልም ሆነ ለመጠየቅ ዶ/ር ታደሰ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ አይደሉም ይለናል። የድምፅ ዘገባውን ይከታተሉ
https://youtu.be/ezWpL115bwc