
የብሄር ማንነት ጥያቄ በኢትዮዽያ ፖለቲካ ውስጥ ዋና መገለጫ ከሆነ ሰነባብቷል። ታዲያ የብሄር ጥያቄን መቀልበስ ይቻላልን? አንዳንድ በማንነት ፖለቲካ ረድፍ የተሰለፉ አስተያየት ሰጪዎች- የሰሜኑ የባህልና የፖለቲካ የበላይነት በሰፈነበት ስርዓት ውስጥ – አሁን ያለችው ኢትዮጵያ ፈርሳ ካልተሰራች የብሄር እኩልነት ሊመጣ አይችልም ሲሉ ይከራከራሉ። ሀገር አፍርሶ መስራቱ ይቻላልን? ይህንና ይህን በመሰሉ ከናንተው በተነሱ ጥያቄዎች ዙሪያ ለዛሬ ያሰናዳነውን ውይይት አድምጡት- አጋሩ- ተሳተፉ።
ቀደም ባሉት ሳምንታት የተላለፉት ክፍል አንድና ሁለትን በማስፈንጠሪያው ያገኟቸዋል
ኢትዮዽያውያንስ ሀገራቸው የት ነው? (ክፍል አንድ) http://wazemaradio.com/?p=1972
ኢትዮዽያውያንስ ሀገራቸው የት ነው? (ክፍል ሁለት) http://wazemaradio.com/?p=2006