obama

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ የምስራቅ አፍሪቃ ጉብኝት ወቅት የሽብር ጥቃት ለማካሄድ የተያዘ ሴራ መኖሩን የዋሽንግተን የደህንነት ምንጮች አመለከቱ። አሜሪካ ዜጎቿ ብርቱ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ፣ ከተቻለም ህዝብ ወደ ተሰበሰበበት አካባቢ ዝር እንዳይሉ መክራለች። በተለይ በኬንያ የሚካሄደውና ፕሬዝዳንቱ የሚካፈሉበት የኢኮኖሚ ኮንፈረንስ የሽብር ጥቃቱ ዋና ኢላማ ሊሆን እንደሚችል የአሜሪካ ውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት አመልክቷል።