11778042_10207119516295144_631979512_n

የኢትዮቴሌኮም ድረ ገጽ በሐከሮች ተጠቃ። ሳሚ ቺቺሮቮ ብሎ ራሱን የጠራ አካል ሐክ ማድረጉን በድረ ገጹ ላይ አስታውቋል። የሰበራው (ሐኪንጉ) ዓላማ አልታወቀም። የኢትዮቴሌኮም ዋና ገጽ የትሮጃን ፈረስ የተባለውን አደገኛ ቫይረስ መሸከሙን የዋዜማ ሙከራዎች አረጋግጠዋል። HTML: Defacement-V [Trj] የተባለው ይህ ቫይረስ ድረ ገጹን በመክፈት ብቻ ሊጋባ ይችላል፣ ከዚያም የተከፈተበትን ኮምፒውተር (ስልክ) በቁጥጥር ስር ያውለዋል። ከዋና ገጹ ውስጥ ያሉት ክፍሎች ለጊዜው ይከፈታሉ፣ ሆኖም ከቫይረሱ ነጻ ናቸው ማለት አይቻልም። ድርጅቱ ችግሩን እስኪፈታ ድረ ገጹን ከመክፈት እንዲቆጠቡ ይመከራሉ። ባለፈው ወር የኢትዮዽያ የብየነ መረብ ድህንነት ተቋም INSA የስለላ ቴክኖሎጂ ያቀርብለት የነበረው የጣልያኑ ሀኪንግ ቲም ኩባንያ ተመሳሳይ ጠለፋ( ሀኪንግ )ገጥሞት ገመናው አደባባይ መዋሉ ይታወሳል።