- ከግጭቱ ሁለት ቀናት በፊት የኤርትራ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር አልጀሪያ ነበሩ? ለምን ዓላማ?
- ኢትዮጵያ በአልሸባብ ጥቃት ወቅት “ምንጩ ያልታወቀ የጦር መሳሪያ ማርኬያለሁ” ብላለች፣ ይህ መረጃ ከሳምንት በኋላ ለተከሰተው ግጭት ግብዓት እንዲሆን የታለመ ነበርን?
ዋዜማ ራዲዮ- የሰሞኑ የኢትዮጵያና የኤርትራ የድንበር ግጭት ወደ ለየለት ጦርነት ያመራ ይሆን? የሚል ትልቅ ስጋት አለ። ግጭቱን ተከትሎ ሁለቱም ሀገሮች በሰፊ የፕሮፓጋንዳ ስራ ተጠምደዋል። በድንበር አካባቢ አሁንም ከፍተኛ ወታደራዊ እንቅስቃሴ መኖሩን መረጃዎች ያመለክታሉ። ለሁለቱ ድሀ ሀገሮች ጦርነት ሊያስከትል የሚችለውን ጣጣ ከወዲሁ መተንበይ ቀላል ነው። ታዲያ ስለምን ጦርነቱ አይቀሬ ይመስላል? ከጦርነቱ ማን ምን ያተርፋል? አርጋው አሽኔ እነዚህ ሁለት ሀገራት ለምን አላማና ግብ ወደ ጦርነት ሊሄዱ አልያም ላይሄዱ ይችላሉ? የሚለውን ከሰሞነኛ የዲፕሎማቲክ ወሬዎች ጋር አስናስሎ አሰናድቶታል። እነሆ ያድምጡት