Siraj Fegessa, Minster of Defense
Siraj Fegessa, Minster of Defense

ዋዜማ ራዲዮ- በኢትዮጵያ የተቀጣጠለውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የኢሕአዴግ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ያወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማስፈጸሚያ ዝርዝር መመሪያ ቅዳሜ ጥቅምት 5 ቀን 2ዐዐ9 ይፋ ሆኗል፡፡

ዳንኤል ድርሻ መንግስት ያወጣውን መግለጫ ዓብይክፍሎች ተመልክቶታል። ዘገባውን በድምፅ እዚህ ያገኙታል

የማስፈጸሚያውን ዝርዝር ለጋዜጠኞች ያቀረቡት የኮማንድ ፖስቱ ሴክሬታሪያት እና የመከላከያ ሚኒስትር ሲራጅ ፈጌሳ ሲሆኑ፣ ዝርዝሩን በንባብ ያቀረቡት ሌተና ኮሎኔል ሞገስ ሃብቱ ናቸው፡፡ የኮማንድ ፖስቱ መመስረት ተጠቅሶ ለከፍተኛ ወታደራዊና የፖሊስ መኮንኖች ትዕዛዝ በተላለፈበት ዕለት ከአቶ ሲራጅ ፈጌሳ በስተቀኝ የተቀመጡት ኤታማዦር ሹሙ ጀኔራል ሳሞራ የኑስ ነበሩ፡፡ ከአንድ ቀን በፊት ማለትም ባለፈው አርብ ጥቅምት 4 ቀን 2009 ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ጌታቸው አምባዬ፥ የደንቡ ማስፈፀሚያ መመሪያ በአጭር ጊዜ ውስጥ ነበር ያሉት፡፡ እሳቸው በቅርብ ጊዜ ይወጣል ያሉት የማስፈጸሚያ ዝርዝሩ በማግስቱ ቅዳሜ ይፋ ተደርጓል።

ባለ 31 አንቀጹ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማስፈጸሚያ ዝርዝር ሶስት አብይ ክፍሎች ያሉት ሲሆን፣ አብላጫውን ከፍል የያዘው የክልከላና “ይሕን አታድርግ” የሚለው የመብት ግደባ ዝርዝር ነው፡፡ የተከለከሉ ድርጊቶች ተፈጽመው ሲገኙ “ማንኛውም እርምጃ” እንደሚወሠድም ይገልጻል፡፡

“ማንኛውም ሁከት፣ ብጥብጥና በሕዝቦች መሃከል መቃቃርና መጠራጠር የሚፈጥር ይፋዊም ሆነ ድብቅ ቅስቀሳ በማናቸውም መልኩ ማድረግ፤ ጽሑፍ ማዘጋጀት፣ ማተምና ማሰራጨት፣ ትዕይንት ማሳየት፣ በምልክት መግለጽ፣ ወይም መልዕክትን በማናቸውም በሌላ መንገድ ለሕዝብ ይፋ ማድረግ፣ ፈቃድ ሳይኖር ማንኛውንም ሕትመት ወደሃገር ውስጥ ማስገባት ወይም ወደ ውጪ ሃገር መላክ” በይፋ መታገዱን የሚጠቁመው መመሪያው “መልዕክት በኢንተርኔት፣ ሞባይል፣ በጽሑፍ፣ በቴሌቪዥን፣ በሬዲዮ፣ በማሕበራዊ ሚዲያ ወይም በሌሎች የግንኙነት ዘዴዎች መለዋወጥ” በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን ይገልጻል፡፡

የአሸባሪ ድርጅቶችን የተለያዩ ጽሑፎች መያዝ፣ ማሠራጨት፣ አርማቸውን መያዝ ወይም ማስተዋወቅ” እንደማይፈቀድ የሚዘረዝረው ማስፈጸሚያው የቴሌቪዥን ወይም የሬዲዮ ፕሮግራምን መከታተል በሚከለክለው ክፍሉ “እንደ ኢሳት፣ ኦኤምኤን እና የመሳሰሉትን የሽብርተኛ ድርጅቶችን ሚዲያዎች ማሳየት፣ መከታተል፣ ሪፖርት ማድረግ የተከለከለ ነው” ይላል፡፡ ማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ የሀገርንሉዓላዊነት፣ ደህንነት እና ሕገ መንግስታዊ ሥርዓትን የሚጎዳ ማናቸውም ጋዜጣዊ መግለጫ ለሀገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ሚዲያዎችመስጠትም ከዚህ በኋላ በጥብቅ የተከለከለ ሆኗል።

ዲፕሎማቶች ከአዲስ አበባ ዙሪያ 4ዐ ኪሎሜትር ርቀው መሄድ እንደማይገባቸው የገለጹት አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ይሕ የተወሰነው ለሌላ ዓላማ ሳይሆን ለራሳቸው ለዲፕሎማቶች ደሕንነት ሲባል መሆኑን ካስረዱ በኋላ ከዚህ ርቀት ውጪ ለመውጣት ጠይቀው፣ በኮማንድ ፖስቱ የሚፈቀድላቸው ከሆነ ወይ አጃቢ ይመደብላቸዋል አለያም ኃላፊነቱን ራሳቸው ይወስዳሉ ብለዋል፡፡ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ እና የኮሙኒኬሽን ሚኒስትሩ ጌታቸው ረዳ ባለፈው ማክሰኞና ረቡዕ አዲስ አበባ የሚገኙ የውጪ ሃገራት ዲፕሎማቶችን ባናገሩበት ወቅት ግን ስለዚህ ጉዳይ የተነሳ ጉዳይ አልነበረም፡፡

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማስፈጸሚያ ዝርዝር መመሪያው የንግድ ስራዎች፣ ሱቆች፣ ወይም የመንግስት ተቋማት መዝጋት ወይም ምርትእና አገልግልት ማቋረጥ፣ ከስራ ቦታ ያለበቂ ምክንያት መጥፋት ወይም ስራ ማቆም፣ ተገቢውን አገልግሎት አለመስጠት እና ስራ መበደልክልክል መሆናቸው ነው የተገለጸው።

በሃይማኖታዊ ተቋማት ውስጥ በሚደረጉ ስብከቶች እና ትምህርቶች ሃይማኖታዊ አስተምህሮ ከማስተማር ውጪ በህዝቦች መካከል መጠራጠር እና መቃቃርን የሚፈጥር፣ በህብረተሰቡ ላይ ስጋት ፣ ሁከት እና ብጥብጥየሚፈጥር ቅስቀሳ እንዳይደረግ ተብሏል።

“በትምህርት ቤቶች፣ በዩኒቨርሲቲዎች እና በሌሎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር ሂደትን የሚያውክ አድማ ማድረግ፣የትምህርት ተቋማትን መዝጋት ወይም በነዚህ ተቋማት ላይ ጉዳት ማድረስ የተከለከለ ነው።” ሲል የደነገገው መመሪያው “በትምህርትቤቶች እና በሌሎች ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ አድማ የሚያደርጉ ሰዎችን ለመያዝ እና ችግሩን ለማስቆም የህግ አስከባሪ አካላትበተቋማቱ ውስጥ በመግባት አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ ይችላሉ።” ሲል አስፍሯል፡፡

በስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከላት፣ ከስፖርታዊጨዋነት ውጪ የሆኑ ሁከቶችን፣ ብጥብጦችን መፍጠር ጥብቅ ክልከላ ተጥሎበታል። በዛቻ እና በሌሎች መሰል ድርጊቶች ሰላማዊእንቅስቃሴን ማወክ፣ አገልግሎት ማስተጓጎል፣ የመጓጓዣ ዋጋ ታሪፍ መጨመር፣ የሚመለከተው አካል ከደለደለደው የስራ ስምሪት ውጪመሆን፣ የእግረኛ እና ሌሎች የመጓጓዣ ዘዴዎችን እንቅስቃሴ መንገድ መዝጋት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መመሪያው ትኩረት ያደረገበት ሌላው ክፍል ሆኗል።

የሕግ አስከባሪ ኃይሎችን የደንብ ልብስ (ዩኒፎርም) መልበስ፣ ይዞ መገኘት፣ ቤት ማስቀመጥ፣ አሳልፎ መስጠት እና መሽጥ ክልክል መሆኑን ክልክል ነው ያለው ዝርዝሩ “ማንኛውም የሕግ አስከባሪ አካላት ባልደረባ ወይም ማንኛውም ሕጋዊ ትጥቅ ያለው ሰው ትጥቁንበማንኛውም ሁኔታ በሶስተኛ ሰው እጅ እንዲገባ ማድረግ የተከለከለ ነው ሲል አስጠንቅቋል።

ማንኛውም የሕግ አስከባሪ አካል ባልደረባ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተፈጻሚ በሚሆንበት ጊዜ ከስራ መልቀቅ ወይም አስገዳጅ ሁኔታ ካልተፈጠረ በስተቀር የዓመት እረፍት ፈቃድመውሰድን በመመሪያው የተከለከለ ነው። በመመሪያው የተከለከሉ ተግባራትን በማለፍ ሕገ ወጥ ድርጊት የሚፈጽሙ ሰዎችን፣ በገንዘብእና በቁሳቁስ ወይም በማናቸውም ሌላ መንገድ መደገፍ እንዲሁም ከለላ መስጠት፣ መደለያ መስጠት እና ማበረታታትም አይፈቀድም፡፡

ከኢትዮጵያ ድንበር 50 ኪሎ ሜትር ወደ ውስጥ ገባ ብሎ የክልከላ “ቀይ ዞን” ተብሎ መለየቱን፣ እንዲሁም በዘጠኝ የተለያዩ ቦታዎች ማለትም፥ ከአዲስ አበባ ጂቡቲ፣ ከአዲስ አበባ ሻሸመኔ ዶሎ፣ ከአዲስ አበባ ሐረር፣ ከአዲስ አበባ አሶሳ፣ ከአዲስ አበባ ጋምቤላ፣ ከአዲስ አበባገብረጉራቻ፣ ከጎንደር መተማ፣ ከጎንደር ሁመራ፣ ከአዲስ አበባ ሻሸመኔ ሞያሌ ዋና መንገዶች 25 ኪሎ ሜትር ወደ ቀኝ እና 25 ኪሎ ሜትርወደ ግራ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ መሆኑን ሴክሬታሪያቱ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ አብራርተዋል፡፡ በነዚህ ስፍራዎች የጦርመሳሪያ ይዞ ከመንቀሳቀስ ባሻገር፣ በልማት አውታሮች እና በመሰረተ ልማቶች ላይ ጥቃት መሰንዘር እና ሁከትን ለማስቆም እና አደጋንለመከላከል የሚደረግ እንቅስቃሴን ማወክ ክልከላ ተደርጎባቸዋል።

የኢኮኖሚ አውታሮች፣ መሰረተ ልማትና የኢንቨስትመንት ተቋማት፣ የእርሻ ልማቶች፣ ፋብሪካዎችና መሰል የልማት ተቋማት አካባቢ ከቀኑ12 ሰዓት እስከ ንጋት 12 ሰዓት ድረስ ከተፈቀደለት ሰራተኛ በስተቀር ማንኛውም ሌላ ሰው መንቀሳቀስንም እንደማይችል፣ የሠዓትእላፊውን ተላልፎ በተገኘ ማንኛውም ሰው ላይ የጥበቃ ወይም የሕግ አስከባሪ አካላት አስፈላጊውን እርምጃ የመውሰድ ሥልጣንእንደተሰጣቸውም ተገልጿል።

በሌሎች ቦታዎች በኮማንድ ፖስቱ ውሳኔ የሰዓት እላፊ በይፋ በሚገለጽበት ቦታና ጊዜ የሰዓት እላፊ ክልከላንበመተላላፍ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ አይፈቀድም ተብሏል። ሰላምና ፀጥታን ሊያደፈርሱ ይችላሉ ተብለው የሚጠረጠሩ ሰዎች ወይምቡድኖች ወይም ለጉዳት ተጋላጭ ናቸው ተብለው የሚገመቱ ሰዎች ወይም ቡድኖች ወደተወሰነ አካባቢ ወይም ህንፃ እንዳይገቡ ወይምበተፈቀደላቸው አንድ የተወሰነ አካባቢ ብቻ እንዲቆዩ የተሰጠን ትእዛዝ መተላለፍ አይቻልም።

ተሃድሶ እና ፍርድ ቤት ማቅረብን በተመለከተው የመመሪያው ዝርዝር ሰው የገደለን ጨምሮ በነውጥ ላይ ተሳትፈዋል የተባሉ አካላት ትምሕርት ተሠጥቷቸው ሊለቀቁ ይችላሉ ብሏል፡፡ ማስፈጸሚያ መመሪያው ስለዚሁ ሁኔታ በሚያብራራበት ክፍል እንዲሕ ይላል፤

– በሕግ መሰረት በኮማንድ ፖስቱ የሚደረግ የተሃድሶ እርምጃዎች እንደሚኖሩ በተጠቀሰበት የአዋጁ ድንጋጌ፤ ኮማንድ ፖስቱ ለፍርድመቅረብ ያለበትን እንዲቀርብ ያደርጋል፤

– ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ በተፈፀሙ የሁከት እና የነውጥ እንቅስቃሴዎች ላይ በቡድን ወይም በግል የተሳተፈ፣

– የጦር መሳሪያ ሳይዝ የመንግስትም ሆነ የግለሰብን ንብረት የዘረፈ እና የዘረፈውን መሳሪያ እና ንብረት ይህ መመሪያ ከወጣ በኋላ ባሉትአስር ቀናት ውስጥ በአቅራቢያው ላለ ፖሊስ ጣቢያ የመለሰ እና እጁን የሰጠ ፤

– ከዚህ በፊት ለሕገ ወጥ ተግባራት የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ ያደረገ፣ ወረቀት በመበተን፣ አድማ በማድረግ የተሳተፈ እና ያነሳሳ፣ ሰውየገደለ፣ ማንኛውንም ንብረት ያቃጠለ፣ ማንኛውንም ወንጀል የፈፀመ ሰው፤ ይህ መመሪያ ከወጣ በኋላ ባሉት 10 ቀናት ውስጥበአቅራቢያው ላለ ፖሊስ ጣቢያ የመለሰ እና እጁን ከሰጠ፤

እንደ የወንጀል ተሳትፎው ቀላል እና ከባድነት ዋና ፈፃሚ እና አባሪ ተባባሪ መሆኑ ታይቶ፣ በኮማንድ ፖስቱ የተሃድሶ ትምህርትተሰጥቶት እንዲለቀቅ ይደረጋል።