Dr Mulatu Teshomeዋዜማ ራዲዮ- የኢትዮጵያ መንግስት አዲሱን አመት ምክንያት በማድረግ ለ707 የፊደራል መንግስት ታራሚዎች ምህረት መስጠቱን ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ ይፋ አደረጉ።

ከቀናት በፊት የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊዎች ክስ ጋር በተያያዘ ሶስት እስረኞች ይፈታሉ የሚል መረጃ ለታሳሪ ቤተሰቦች መነገሩ ተሰምቷል ።
በፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ የዛሬ የይቅርታ መግልጫ ላይ ዝርዝር ነገር አልተካተተም።የፖለቲካ እስረኞች ምህረት ከተደረገላቸው ዝርዝር ውስጥ ስለመኖራቸውም ምንም ፍንጭ የለም።

ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሆኑት አቶ ጌታቸው አምባዬም ነገ ጳጉሜ 5 ምህረት የተደረገላቸውን እስረኞች አስመልክተው በሰንዳፋ ፓሊስ ኮሌጅ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የዋዜማ ምንጮች ጠቁመዋል። [ዝርዝሩን እንዳገኘን እናክልበታለን]