Remittances_2

የኢትዮጵያ መንግስት ዲያስፖራው ጥሪቱን ወደ ኢትዮጵያ ፈሰስ እንዲያደርግ የተቻለውን ሁሉ ጥረት ያደርጋል፣ ከባህር ማዶ ወደሀገር ቤት የሚላከው የገንዘብ መጠንም (Remittance)ቀላል አይደለም። ይሁንና ግን መንግስት የዲያስፖራውን ገንዘብና ሀብት መቀራመት እንጂ መሰረታዊ የፖለቲካ ተሳትፎ መብቶች አልፈቀደም። የጥምር ዜግነትን ከመከልከል ጀምሮ ዲያስፖራው በሀገሩ ልማትና የዴምክራሲ ስርዓት ለማምጣት አልተፈቀደለትም። ይልቁንም የመንግስትና የዲያስፖራው ግንኙነት ጥርጣሬና ባላንጣነት አረብቦበታል። የዋዜማ ውይይት በዚህ ጉዳይ ላይ አተኩሯል።