ዋዜማ ራዲዮ- ኦሮሚያ ክልል የለፉትን ሁለት አመታት ተከታታይ ተቃውሞዎችን በማድረግ ቀዳሚነቱን የያዘ የሀገሪቱ ክፍል ነው። በርካቶች ሞተዋል ከግማሽ ሚሊያን በላይ ተፈናቅለዋል። ተቃውሞው አሁንም እንደቀጠለ ነው። ለመሆኑ የኦሮሞ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ከየት ተነስቶ የት ደረሰ? የኦሮሞ ህዝብ ትግል በየዘመናቱ የገጠሙት ፈተናዎችስ ምንድን ናቸው? የኦሮምኛ ተናጋሪው አዲስ ትውልድ በተምታቱ ተቃራኒ ስብከቶች መሀከል እየዋለለ ነው። ተከታዩ ዘገባችን የኦሮሞ ህዝብ ትግል የተከፈለውን መስዋዕትነት ያህል ውጤት እንዲያመጣ በግቦቹ ላይ የጠራ አቋም ለመያዝ ጊዜው አሁን ነው ይለናል፣ አርጋው አሽኔ አዘጋጅቶታል

https://youtu.be/hNrJx7z9avc