ዋዜማ- የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ  ፓርቲ (ኢህአፓ)ከተመሰረተ ግማሽ ምዕተ ዓመት አስቆጠረ። ፓርቲው በዛሬይቱ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ቅርፅ ላይ ጉልህ አሻራ ያለው ድርጅት ነው። ፓርቲው ዛሬም አዳዲስ ወጣቶችን አደራጅቶ የፖለቲካ አላማውን ለማስፈፀም እየሞከረ ነው።

ፓርቲው ገናና ከነበረበት የአብዮቱ ዘመን አሁን እስካለበት ጊዜ ድረስ ያለውን እንዲነግሩን የፓርቲው ከፍተኛ አመራር የነበሩትንና በድርጅቱ ምስረታና አካሄድ ላይ ቀልፍ ሚና የነበራቸውን አቶ ክፍሉ ታደሰን የዋዜማው ብስራት ከፈለኝ አነጋግሯቸዋል። ቃለምልልሱን ከታች ያድምጡት።