ዋዜማ ራዲዮ- ከሰሞኑ የአሜሪካ የሰለላ ተቋም አንዱ የሆነው ናሽናል ስኩሪቲ ኤጀንሲ (NSA) ላለፉት አስራ አምስት አመታት ከኢትዮዽያ ጋር ባደረገው ስምምነት የድምፅ ግንኙነትን ለመጥለፍ የሚረዱ ዘመናዊ መሳሪያዎችን በማስታጠቅ በጋራ ሲሰራ መቆየቱ ተጋልጧል። ይህን ቴክኖሎጂ የኢትዮጵያ መንግስት ተቀናቃኞቹን ለማጥቃት ይጠቀምበታል የሚል ስጋት ያላቸው ወገኖችም ጉዳዩ አሳሳቢ መሆኑን እየተናገሩ ነው።

አሜሪካ ይህን ትብብር በሶማሊያ ና በአካባቢው ሀገሮች ላይ ስለላ ለማካሄድ የምትጠቀምበት ሲሆን NSA በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ቢሮ ከፍቶ ሲሰራ እንደነበረም ምስጢራዊ መረጃዎችን በማተም የሚታወቀው The Intercept የተባለ ድረገፅ አጋልጧል። ሰለጉዳዩ ተጨማሪ መረጃዎችን ስናሰባስብ ነበር፣ እስቲ አድምጡት

https://youtu.be/ZPkwRC-6Hn0