ዋዜማ ራዲዮ- ከቅዳሜ አመሻሽ ጀምሮ የሳዑዲ መንግስት በወሰደው እርምጃ ከሀገሪቱ ልዑላውያንና ባለሀብቶች ጋር አብረው የታሰሩት የሼክ መሀመድ አላሙዲንን ጨምሮ የታሳሪዎቹ የባንክ ሂሳብ መታገዱ ተሰማ።
የሳዑዲ መንግስት ባስተላለፈው ውሳኔ ታሳሪዎቹ ገንዘብ እንዳያንቀሳቅሱ ከማገድ በተጨማሪ በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል ዙሪያ ምርመራ እየተደረገ መሆኑም ተነገሯል።
እግዱ በሳዑዲ ብቻ ያላቸውን ገንዘብ የሚመለከት ይሆን አለማቀፍ እግድ አልተብራራም።

እስሩ ከሙስና ይልቅ በሳዑዲ ንጉሳውያን ቤተሰቦች መካከል ባለው የፖለቲካ ሽኩቻ ሳቢያ መሆኑ ጎልቶ እየተሰማ ነው።

ሼክ አላሙዲ ከሌሎቹ ታሳሪዎች ጋር እጅግ ውድ በሆንው ሪዝ ካርልተን ሆቴል ውስጥ ጥበቃ እየተደረገላቸው ነው። የተወስኑ ወዳጆቻቸው እንደጎበኟቸውም ተሰምቷል።
ከአዲስ አበባ የቅርብ ወዳጆቻቸው ሊጎበኟቸው ወደዚያው እንዳቀኑ ከሚድሮክ ግሩፕ አካባቢ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። የተወሰነ የስልክ አገልግሎትም ተፈቅዶላቸዋል።