ዋዜማ ራዲዮ- የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ መንበር አቶ የሽዋስ አሰፋ ትላንት ሰኞ ግንቦት 14 ቀን ከወንጀል ምርመራ በደረሳቸው ጥሪ መሰረት ፓሊስ ጣቢያ ሲሄዱ ከዚህ በፊት ነፃ በተባሉበት ክስ በፍርድ ቤት እንደሚፈለጉ ተነግሯቸው ፍርድ ቤት መቅረባቸውን የዋዜማ ዘጋቢ ለማረጋገጥ ችላለች።
ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ የቀረቡት አቶ የሽዋስ ከፍ/ቤት ለፓሊስ በተላለፈው የክስ ጥሪ ወረቀት ላይ በእነ አቶ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ እንደሚፈለጉ የተጠቀሰ ሲሆን ግለሰቡ ፍ/ቤት ከቀረቡ በኃላ በ4ኛ ወንጀል ችሎት የመሀል ዳኛ አማካይነት አቶ የሽዋስ በስህተት የተጠሩ መሆኑ ተነግሯቸዋል ።
አቶ የሽዋስ በአጋጣሚ እሩቅ ሆነው እንጁ ከወንጀል ምርመራ እንደሚፈለጉ ሰኞ በደረሳቸው ጥሪ መሰረት ወዲያውኑ ፓሊስ ጣቢያ ቀርበው ቢሆን ኖሮ በእስር ያድሩ ነበር
ከአመታት በፊት አቶ የሽዋስ አሰፋ ከአንድነት ፓርቲና ከሌሎች ፓለቲከኞች ጋር በእስር ከቆዩ በኃላ በፍ/ቤት አቶ ሀብታሙ አያሌውን ጨምሮ ዳንኤል ሽበሽና አብርሃ ደስታ ነፃ ናችሁ በተባሉ ጊዜ አቶ የሽዋስ አሰፋም ነፃ ተብለው ወደ ፓርቲ ሊቀ መንበርነት መጥተዋል።።
በተከሰሱበት ወንጀል በፍርድ ቤት ነፃ ከተባሉ በኃላ አስቀድሞ የተከሰበት አንቀጽ ተቀይሮ እና የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን የተላለፈ ተግባር ፈፅማችኃል በሚል በእስር ላይ ከሚገኙት መሀከል ዳንኤል ሽበሽ ዛሬ ፍ/ቤት ቀርቦ ጉዩየ ውኔና ሳያገኝ ለሌላ ቀጠሮ ተላልፏል ።