ዋዜማ ራዲዮ-ከተመሰረተ ሁለተኛ አመቱን የያዘውና የተሻለ አፃፃፍና የሀሳብ አቀራረብ ያላቸውን ጋዜጠኞችና ጦማርያን ለማበረታታት የተቋቋመው Rewarding Good Wrting (RGW) የዋዜማን ባልደረባ “ገረመው” በአንደኝነት ሸልሞታል።

ከአዲስ ስታንዳርድ መፅሄት ማህሌት ፋሲልና የዞን ዘጠኝ ጦማሪው ዘላለም ክብረትም ለዚሁ ሽልማት ከታጩት ውስጥ ነበሩ። ሁለተኛና ሶስተኛ በመሆን ተሸልመዋል።
የዋዜማ ራዲዮ ባልደረባ “ገረመው” ለሽልማት የበቃው “ከአሳሪ ወገን ነዎት ወይስ ከታሳሪ” በሚል ለንባብ ያበቃው በመረጃ ላይ የተመስረት ስላቃዊ ፅሁፍ ነው።

ለውድ ድሩ 49 ተወዳዳሪዎች ከ15 የሚዲያ ተቋማት እንዲሁም 34 ጦማርያን ቀርበዋል።

የጋዜጠኝነት ሙያ እንዲዳብር የተጀመረው ይህ የሽልማት ፕሮግራም የተጀመረው በሆላንድ በምትኖር ታሪኳ ጌታቸው የግል ጥረት ሲሆን ለውድድሩ በየአመቱ ገለልተኛ ዳኞች ይሰየማሉ።

Rewarding Good Writing website- http://www.bestofjeth.com/