ዋዜማ ራዲዮበሰሜኑ ጦርነት ሳቢያ በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች በመዘጋታቸው የተፈናቀሉ ወደ 4,000 የሚደርሱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን በሌሎች ክልሎች በሚገኙ ዩንቨርስቲዎች መመደባቸው ዋዜማ ያሰባሰበችው መረጃ ያመለክታል፡፡

በትግራይ ክልል ከሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርሰቲዎች በተለይም መቀሌ፣ አዲግራት፣አክሱም እና ራያ ዩንቨርስቲዎች ዋና ካምፓሶችና ኮሌጆች ውስጥ ሲሰሩ የነበሩት መመህራን ጦርነትቱን ተከትሎ በተደረገ ጊዜዊ ድልዳላ በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ ዩንቨርስዎች በጊዜዊነት ዝውውር መመዳባቸውን ለዋዜማ የገለጹት የኢትዮጵያ መመህራን ማህበር ፕሬዚዳንት  ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

በተመሳሳይ ከዚሁ ክልል በመቀሌና አላማጣ ከተማ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሲሰሩ የነበሩ መምምራን  ሸሽተውና ተፈናቅለው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ቅጥር እንዲፈጸምላቸው  ጥያቄ ያቀረቡ 25 መምህራን እንዳሉ ዮሐንስ  ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጅ የሁለተኛ ደራጃ ትምህርት ቤቶችን ጉዳይ የሚመለከተው የየክልሎቹ ትምህርት ቢሮ በመሆኑ በትምህርት ሚንስቴር በኩል መልስ ባለማገኘታቸው መምራኑ ከመምህራን ማህበሩ ጋር መነጋገራቸውን አክለው ገልጸዋል፡፡

ጦርነቱ ከተጀምረ ጊዜ ጀምሮ ተፈናቅለው አዲስ አበባ የገቡት የሁለተኛ ደረጃ መምሀራን ከትግራይ ክልል ጋር ያለው ችግር እስኪፈታ ቦታ እንዲፈለግላቸው ለኢትዮጵያ መምራን ማህበሩ ያቀረቡትን ጥያቄ መሰረት በማድረግ ማህበሩ ‹‹ አቅም በፈቀድ መጠን ትብብር እንዲደረግላቸው›› መረጃ እየሰነዱ እንደሆነ ፕሬዚዳንቱ ገልፀዋል፡፡

ጉዳዩ ምንም እንኳ አስቸጋሪ ቢሆንም፣ አሁን ያለው ሁኔታ እስኪረጋጋ ድረስ ሪፖርት ያቀረቡትን መምህራን ቢያንስ እንኳ በጊዜዊት ክልሎች ላይ ተመድበው የሚሰሩበት መፍትሄ እንዲያገኙ  ማህበሩ ለጠቅላይ ሚንስቴሩ፣ ለትምህርት ሚንስቴር፣ለገንዘብ ሚንስቴርና ለክልሎች እንደ አማራጭ ጥያቄ እያቀረቡ መሆኑን ዮሃንስ ተናግረዋል፡፡

ዩኒቨርስቲዎችን በበላይ ሲመራ የነበረው  የቀድሞው የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በመስከረም 2014 ዓ.ም አዲስ በተቋቋመው አደረጃጀት መሰረት ወደ ትምህርት ሚኒስቴር የተጠቃለለ ሲሆን የመምህራኖቹ ጉዳይ ለዚሁ ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ መዘዋወሩ የሚታወስ ነው። [ዋዜማ ራዲዮ]