በሀገራችንም ሆነ በመላው ዓለም የማህበራዊ መገናኛ መተግበሪያዎች መስፋፋት ግለሰቦች የፈለጉትን መረጃ እንዲያሰራጩ ዕድል ከፍቷል።


ይህን ተከትሎም የሐሰተኛ መረጃ ስርጭት በግለሰብና በተደራጁ ቡድኖች በስፋት እየተሰራጨ ይገኛል። ይህ ክስተት ለእውነተኛ መረጃ ፈላጊዎችና ለመገናኛ ብዙሀን ትልቅ ፈተና ነው። ዋዜማ ራዲዮ ሐሰተኛ መረጃዎችን ለመለየት እየተደረጉ ባሉ ጥረቶች ከሌሎች ባለድርሻዎች ጋር በትብብር እየሰራች ነው። ከዚህ በታች የቀረቡት የልምምድ ግኝቶች ናቸው። ይህ እውነትን የማጣራት ስራ ዋዜማ ራዲዮ ከኮድ ፎር አፍሪካ (ፔሳቼክ) ጋር በመተባበር ከዶቸቨለ አካዳሚ በተገኘ ድጋፍ የቀረበ የተሰራ ነው፡፡ እነዚህን ዘገባዎች ያጣራችው ሰላም ተሾመ ናት።

ሐሰት፡-ቪዲዮው የአርቲስት ሙሉአለም ታደሰን የቀብር ስነ ስርአት አያሳይም

በመረጃ ማዕድ በዩቲዩብ ቪዲዮ ላይ የቀረበው ሙሉአለም ታደሰ የስራ እና የህይወት ታሪክ ነው፡፡

በዩቱዩብ ቪዲዮው ላይ የአርቲስት ሙሉአለም ታደሰን የቀብር ስነ ሥርዓት ያሳያል በሚል የተለቀቀው ቪዲዮ ሀሰት ነው፡፡

መረጃ ማዕድ በተባለ የዩቱዩብ ቻናል ላይ “ ሳናስበው አመለጠችን” “የአርቲስት ሙሉአለም ታደሰ የቀብር ስነ ስርዓት”  “ብዙዎችን ያስደነገጠው የአርቲስት ሙሉአለም ታደሰ ሞት ምክንያት” የሚል ርእሶችን በ ምስል ላይ ይዞል፡፡

ይህን ቪዲዮ ከ300ሺህ በላይ ሰዎች ተመልክተውታል፡፡ አስተያየት መስጫው ሳጥን አስተያየት እንዳይሰጥበት ተዘግቶል፡።

11 ደቂቃ ከሃያ ሰከንድ በሚረዝመው በዚህ ቪዲዮ የቀረበው የቀብር ስርዓት ሳይሆን የአርቲስት ሙሉአለም ታደሰ የስራ እና የግል ታሪኮች ናቸው፡፡ 

የአርቲስት ሙሉአለም ታደሰን የቀብር ስነ ስርዓት ያሳያል በሚል የቀረበውን የዩቲዩብ ቪዲዮ ተመልክተን ሐሰት መሆኑን አረጋግጠናል

======================================================================

ሐሰት፡-ይህ ምስል የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የቴሌቭዥን መስኮት ምስል የኢትዮጰያ እና የኤርትራ መሪን ሲመለከቱ አያሳይም

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከነጩ ቤተመንግስት ሆነው ናሳ በማርስ ላይ ያደረገውን ስኬታማ ጉዞ እየተመለከቱ ነበር፡፡

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የቴሌቭዥን መስኮት ምስል ላይ የኢትዮጲያ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ እና የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን ሲመለከተ የሚያሳየው የፌስ ቡክ ልጥፍ ሐሰተኛ ነው፡፡

ኤርትራ ፕረስ በተባለው የፌስ ቡክ ገፅ ላይ የተለጠፈው ይህ ምስል የ ‘Special relationship’ ወይም ልዩ ግንኙነት በሚል የተለጠፈ ሲሆን  ከስምንት ሺህ በላይ ሰዎች ስሜታቸውን ገልፀውበታል ፣ሁለት መቶ ሰማንያ ሰዎች ተጋርተውታል፣ አንድ መቶ ሰባ ስድሰት ሰዎች አስተያየት ሰጥተውበታል፡፡

የሪቨርስ ኢሜጅ ፍለጋ ውጤት እንደሚያሳየው ከሆነ  ምስሉ የተወሰደው ጆ ባይደን በቲውተር ገፃቸው ላይ ናሳ በተሳካ መልኩ ወደ ማርስ ያደረገውን ጎዞ በተመለከተ ባስተላለፉት መልዕክት ላይ ተያይዞ የቀረበ ሲሆን ሁኔታውን ሲከታተሉት እንደነበርም ያሳያል፡፡

በፌስቡክ ልጥፍ ላይ የቀረበው የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መሪዎች ሰንደቅ ዓላማ ሲሰቅሉ የሚያሳየው ፎቶ በፍራንስ 24 ዜና ላይ ኤርትራ ዳግም በኢትዮጵያ ኤንባሲዋን መክፈቷን ተከትሎ በቀረበ ዜና ላይ የቀረበና ሀምሌ 13 2018 ሲሆን ሚካኤል ተወልደ በተባለ ፎቶግራፈር መነሳቱን ያሳያል፡፡

በፌስቡክ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት በቴሌቪዥን ስክሪን የኤርትራ እና የኢትዮጵያ መሪውችን ሲመለከት የሚያሳየውን ፎቶ ተመልክተን ባደረግን የእውነት ማጣራት ሂደት ልጥፉ ሐሰት መሆኑን አረጋግጠናል፡፡

=====================================================

ሐሰት፡- በኢትዮጵያ  ሰራዊት መሳሪያዎች እንደተማረኩ ተደረጎ የቀረበው ምስል ሐሰተኛ ነው

ምስሉ በቡሩንዲ ሙራምቪያ ውስጥ ትጥቅ የማስፈታት እና መልሶ የማቋቋም ስራ በይፋ በተጀመረበት ወቅት መሳሪያዎች ሲቃጠሉ የሚያሳይ ነው

በፌስ ቡክ በኢትዮጰያ ሰራዊት እንደተማረከ ተደረጎ የቀረበው  ምስል ሀሰት ነው። 

በኢትዮጲያ መንግስት እና  ህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) መካከል እየተደረገ ባለው ጦርነት በሁለቱም ወገን በተለያዩ ጊዜያት ከተዋጊዎች መሳሪያዎችን እንደማረኩ ሲገልፁ ቆይተዋል፡፡  ይህ በፌስ ቡክ የተለጠፈው ምስል  በቡሩንዲ ሙራምቪያ ውስጥ ትጥቅ የማስፈታት እና መልሶ የማቋቋም ስራ በይፋ በተጀመረበት ወቅት መሳሪያዎች ሲቃጠሉ የሚያሳይ ነው፡፡

በጎግል የምስል መፈለጊያ ላይ የተገኘው ውጤት የሚያሳው በኢትዮጵያ ሰራዊት እንደተማረከ ተደርጎ በፍስቡክ ላይ የተለጠፈው  ምስል  ከኢትዮጰያ ጋር የተያያዝ አይደለም።  ምስሉ በቡሩንዲ ሙራምቪያ ውስጥ ትጥቅ የማስፈታት እና መልሶ የማቋቋም ስራ በይፋ በተጀመረበት ወቅት መሳሪያዎች ሲቃጠሉ  የሚያሳይ ነው፡፡ ይህ ምስል ከአራት አመት በፊት ሀምሌ 6 2017 relief ድረገፅ ላይ የታተመ ነው፡፡

በፌስቡክ ላይ የቀረበው ልጥፍ  በኢትዮጲያ ሰራዊት ዛሬ የተማረከ ጠመንጃን የሚያሳይ ነው ተብሎ ቢቀርብም በቡሩንዲ ሙራምቪያ ውስጥ ትጥቅ የማስፈታት እና መልሶ የማቋቋም ስራ በይፋ በተጀመረበት ወቅት መሳሪያዎች ሲቃጠሉ  የሚያሳይ መሆኑን  ባደረግነው እውነት ማጣራት ስራ ተመልክተናል፡፡የፌስቡክ ልጥፉ ሀሰት መሆኑን አረጋግጠናል፡፡ 

ይህ እውነትን የማጣራት ስራ ዋዜማ ራዲዮ ከኮድ ፎር አፍሪካ ጋር በመተባበር የተሰራ ነው፡፡

===================================================================

ሐሰት፡ ይህ ምስል በወሎ ግንባር የተወሰደን የኢትዮጵያ አየር ሀይልን እርምጃ አያሳይም

የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን ድርጀት (ኔቶ) ጦር  ያደረገውን ልምምድ ከሚያሳይ ቪዲዮ ላይ የተወሰደ ምስል ነው፡፡   

በወሎ ግንባር የኢትዮጵያ አየር ሀይል እርምጃ ሲወስድ ዋለ በሚል የቀረበው ምስል ሐሰተኛ ነው ፡ ፡

የፌስቡክ ልጥፉ “በወሎ ግምባር አየር ሀይሉ ወራሪውን ሀይል በዚህ ልክ ነው ድባቅ ሲመታው የዋለው!!” ይላል፡፡

የኢትዮጲያ መንግስት የተናጠል የተኩስ አቁም በማወጅ ሰራዊቱን ከትግራይ ክልል አስወጥቻለው ማለቱን ተከትሎ (ህወሓት) ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ትግራይን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥርዋል፡፡ ህወሓት በሰሜን ወሎ፣በሰሜን ጎንደር እና በደቡብ ጎንደር ዞኖች ወረራን እንደፈጸመ የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አገኘሁ ተሻገር አስታውቀዋል፡፡

በህወሓት ሀይሎች እና በመንግስት መካከል እየተደረገ በሚገኘው ጦርነት ዜጎች እየተፈናቀሉ ስለመሆኑ ይገለፃል፡፡

የጎግል የምስል መፈለጊያ ውጤት  እንደሚያሳየው ከሆነ ዘሰን “ the sun” በተባለው ድረ-ገፅ ላይ በተለያዩ ጊዜያት ከኔቶ ጦር ጋር በተያያዘ በቀረቡ ዘገባዎች ላይ በቪዲዮ ቀርቧል፡፡

ምስሉ የተወሰደበት ቪዲዮ ከኔቶ ጦር የማጠቃለያ ልምምዱን  በሮማኒያ ቺንኩ አካባቢ ሲያደርግ የሚያሳይ ነው፡፡

ባደረግነው የሐቅ ማጣራት በፌስቡክ በወሎ ግንባር የኢትዮጵያ አየር ሀይል እርምጃ ሲወስድ ያሳያል የተባለው ምስል ሐሰተኛ ነው ፡ ፡

============================================================

ሐሰት፡- ምስሉ ከመቀሌ በስተምስራቅ   የተፈፀመን የአየር ጥቃት አያሳይም፡፡

 ትግራይ ክልል በመቀለ በስተምስራቅ በኢትዮጰያ አየር ሀይል በድሮን የተወሰደ ጥቃትን ያሳያል ተብሎ የቀረበው የፌስቡክ ልጥፍ ሐሰት ነው፡፡

 በአማርኛ የተፃፈው ልጥፉ እንዲህ ይላል “”የኢፌድሪ አየር ሃይል ድሮን ከመቀሌ በስተምሥራቅ በኩል 3 ነጭ ቪ 8 መኪኖች በፍጥነት እየሄዱ ሳለ በወሰደው መብረቃዊ ጥቃት ተሽከርካሪዎቹ ሙሉ ለሙሉ አወደመ።”

በፌደራል መንግስት እና በህወሃት አማፅያን መካከል እየተደረገ ባለው ጦርነት መንግስት በመቀሌ የአየር ድብደባዎች አድረጎል፡፡

ይሁንና መቀሌ በስተምስራቅ በኢትዮጰያ አየር ሀይል በድሮን የተወሰደ ጥቃትን ያሳያል ተብሎ የቀረበው የፌስቡክ ልጥፍ ትክክል አይደለም። 

የጎግል ሪቨርስ ኤሜጅ የፍለጋ ውጤት እንደሚያሳየው ከሆነ ምስሉ አሜሪካ በኢራቅ ባግዳድ አየር ማረፊያ የኢራኑን ጀነራል ቃሲም ሶሎማኒ ጥር 2020 የተገደሉበትን የድሮን ጥቃት የሚያሳይ ነው፡፡

=====================================

ሐሰት፡- ይህ ምስል በትግራይ አማፂ ሐይሎች ተመቶ የወደቀ ድሮንን አያሳይም፡፡

 ምስሉ የሚያሳየው  በ2020 ታህሳስ 17 በካንቦዲያ የተከሰከሰን ድሮን ነው፡፡

በፌስ ቡክ ገጽ ላይ  በሕወሓት አማፂያን ደሴ አቅራቢያ ተመታ ወድቃለች የተባለች   ድሮንን ለማሳየት የቀረበው ምስል  ሐሰተኛ ነው፡፡

ልጥፉ ላይ ከምስሉ ጋር ተያይዞ  በአማርኛ ቋንቋ የተፃፈው ጽሁፍ  “ሰበር መረጃ  Tks N 54 የተባለችው ቱርክ ሰራሽ የጦር ድሮን በጀግናው TDF ከደቂቃዎች በፊት በጢጣ ፡ ለደሴ ቅርብ ላይ ተመታ ወድቃለች”  ይላል፡ ፡

በመቀጠልም “ኣብይ ኣህመድ ከወራት በፊት በስድስት መቶ ሚሊዮን ዶላር ከቱርክ ከገዛቸው ሶስት የጦር ድሮኖች መከከል TKS N 54 በTDF  ተመታ የወደቀች ሁለተኛዋ የጦር ድሮን ነች።” ሲል አክሎበታል። 

በኢትዮጲያ የሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል የተከሰተው ጦርነት አሁንም እንደቀጠለ ይገኛል፡፡

የኢትዮጲያ መንግስት በመቀለ የተለያዩ አካባቢዎች የአየር ጥቃቶችን ስለመፈፀሙ ገልፆል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ወደ መቀለ የሚያደርጋቸውን የሰብዓዊ ዕርዳታ በረራዎች ከጥቅምት 12  2014 ዓ.ም  ወዲህ ማቆሙን አስታውቆል

የሪቨርስ ኢሜጅ የፍለጋ ውጤት እንደሚያሳየው ከሆነ ምስሉ  እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር  በ2020 ታህሳስ 17 በካንቦዲያ ካሆ ኮንግ የተከሰከሰን ድሮን ያሳያል፡፡

በፌስ ቡክ ገጽ ላይ “በትግራይ መከላከያ ሀይል” ደሴ አቅራቢያ ተመታ ወድቃለች የተባለች   ድሮንን ለማሳየት የቀረበው ምስል  ተመልክተን ባደረግነው ማጣራት ሐሰተኛ መሆኑን አረጋግጠናል፡፡ 

==================================================

የቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶሃን በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ አስተያየት አልሰጡም

ኢትዮጵያ የአባይን ውሃ ብትፈልግ አፍልታ ሲያሻት አቀዝቅዛ መጠቀም ትችላለች በማለት የትሩኩ ፕሬዝዳንት ተናግረዋል የሚለው የፌስቡክ ልጥፍ  ሀሰት ነው፡፡

ኢትዮጵዯ እና ቱርክ የቆየ የዲፕሎማሲ እና የንግድ ግንኙነት አላቸው ፡፡

ሁለቱ ሀገራት አጋርነታቸውን እያጠናከሩ ይገኛሉ፡፡ቱርክ ከአፍሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት በይበልጥ ማጠናከር የጀመረችው ከ2005 ወዲህ ነው፡፡

በቱርክ ፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት የኮምኒኬሽን ዳይሬክተር ድረገፅ ላይም ሆነ በፕሬዝዳንቱ የቲውተር ገፅ ላይ የታላቁ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ የሰፈረ ምንም አይነት ፁሁፍም ሆነ ንግግር የለም፡፡

ኢትዮጵያ የአባይን ውሃ ብትፈልግ አፍልታ ሲያሻት አቀዝቅዛ መጠቀም ትችላለች በማለት የትሩኩ ፕሬዝዳንት ተናግረዋል የሚለው የፌስቡክ ልጥፍ  የተደረገው የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በስልክ መነጋገራቸው ከተገለጸ ከአራት ቀን በኃላ ነው፡፡

የፌስ ቡክ ልጥፎቹ በተደረጉበት ኦገስት 4 እና 5ቱርኩ ፕሬዝዳንት ስለህዳሴው ግድብ ምንም አይነት አስተያየት ለመገናኛ ብዙሃን አልሰጡም በማህበራዊ ትስስር ገጻች ላይም አላስታወቁም፡፡

 ኢትዮጵያ የአባይን ውሃ ብትፈልግ አፍልታ ሲያሻት አቀዝቅዛ መጠቀም ትችላለች በማለት የቱርከ ፕሬዝዳንት ተናግረዋል የሚለው  የፌስቡክ ልጥፍ ተመልክተን ሀሰት መሆኑን አረጋግጠናል።

========================================================================