ዋዜማ ራዲዮ-ባለፉት ቀናት ግንባታው ይፋ የሆነውንና በሶማሊላንድ የሚገኘውን የበርበራ ወደብ ዱባይ ፖርትሰ የተባለ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ኩባንያ ለ30 አመታት በኮንትራት መውሰዱን ተከትሎ ኢትዮጵያ የኢቨስትመንት ድርሻ መግዛቷን የሶማሊላንድ መንግስት አስታወቀ።
ከሶማሊያ ራሷን በመገንጠል ነፃነቷን ያወጀችው ሶማሊላንድ በማንም ሀገር እስካሁን እውቅና አልተሰጣትም።
ከ 444 ሚሊየን ዶላር በላይ ወጪየተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ኩባንያ ዱባይ ፖርትሰ በተሸኘው ሳምንት የበርበራን ወደብ ተረክቧል።  ኩባን ያው 65 በመቶ ድርሻ ሲኖረው ቀሪውን 35 በመቶ የሶማሊላንድና የኢትዮጵያ መንግስት ይወስዳሉ። የኢትዮጵያ ድርሻ 19 በመቶ ነው።

ዘግይቶ በተነገረ መረጃ ደግሞ ለኢትዮጵያ 19 በመቶ ድርሻ የሰጠው ዱባይ ፖርትሰ እንጂ የሶማሊላንድ መንግስት አይደለም ሲሉ አንዳንድ የሶማሊላንድ ባለስልጣናት ተከራክረዋል። የሶማሊላንድ ድርሻ 35 በመቶ ሲሆን ዱባይ ፖርትሰ ካለው 65 በመቶ ድርሻ 19 በመቶ ለኢትዮጵያ ሸጧል ብለዋል።
የጅቡቲን ወደብ የሚያስተዳድረው ራሱ ዱባይ ፖርትሰ በተደጋጋሚ በወደብ መጠቀሚያ ዋጋ ላይ ያደረገው ጭማሪ ለወደብ አልባዋ ኢትዮጵያ ትልቅ ራስ ምታት ሆኖ ቆይቷል።
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስም ሆነች ኢትዮጵያ ከራስ አገዟ ሶማሊላንድ መንግስት ጋር የሚያደርጉት ውል የሶማሊያ ፌደራል መንግስትን ሉዓላዊነት የሚዳፈርና ህገ ወጥ ነው በሚል የሞቃዲሾ መንግስት ተቃውሞውን አሰምቷል። የበርበራ ወደብ በተመረቀበት ወቅት የኢትዮጵያ ሚንስትር የሚመሩት የልዑካን ቡድን በቦታው ተገኝቶ ነበር።