ዋዜማ ራዲዮ- ለሀያ ሰባት ዓመታት በስልጣን ላይ የነበረውንና በህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ህወሐት ይመራ የነበረው መንግስት በለውጥ አራማጆች እጅ እንዲገባ ህዝባዊ ተቃውሞ ከፈጠረው ግፊት በተጨማሪ በራሱ በመንግስት ውስጥ የነበረው ክፍፍል አስተዋፅዖ አድርጓል። ብዙዎች ቲም ለማ በመባል የሚታወቀውን የኦህዴድና የብአዴን አንጃ የሆነውን አብይ አህመድ፣ ለማ መገርሳ፣ ገዱ አንዳርጋቸው ፣ ደመቀ መኮንን፣ አምባቸው መኮንንና ሌሎችም ያሉበትን ቡድን ለለውጡ ያወድሱታል። ግን ደግሞ ስማቸው ገኖ ያልተነገረ፣ እንዳውም ህዝብ የማያውቃቸውና ለለውጡ ዋጋ የከፈሉና ራሳቸውን መስዋዕት ያደረጉ አሉ። ከነዚህ መካከል የብሄራዊ መረጃና ደህንነትና መስሪያ ቤት ትልቅ ፍልሚያ ከተደረገባቸው ተቋማት አንዱ ነው። ሙስናና ብልሹ አሰራርን በማጋለጥ የሚታወቀውና ዛሬ በእስር የሚገኘው ጌታቸው ዋለልኝ ታሪክ ይህ ነው። አድምጡት

https://youtu.be/9ZGoqYoKjmc