Gedu Andargachewዋዜማ ራዲዮ- በአማራ ብሔር ክልላዊ መንግሥት ውስጥ በተነሣው ተቃውሞ ምክንያት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከፖለቲካውሣኔዎች ውጪ መሆናቸውና ሥልጣናቸው ወደ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን መተላለፉ በሰፊው እየተወራ ነው፡፡ ይህን ዘገባ እዚህ በድምፅ ሊሰሙት ይችላሉ- አልያም ንባብዎን ይቀጥሉ

በጐንደር የተነሣውን የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ መነሻ አድርጎ በክልሉ የተቀጣጠለው የህዝብ ቁጣና እምቢታ ከክልሉ አቅምበላይ መሆኑ ርዕሰ መስተዳደሩ ከፖለቲካ ውሣኔዎች ውጪ ለመደረጋቸውእንደምክንያት መሰጠቱን የውስጥ ምንጮች ይናገራሉ፡፡

ስለጉዳዩ የተጠየቁት የክልሉ የኮሚኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ እና ሌሎችም ባለስልጣናት ጉዳዩን ከእውነት የራቀ ነው በሚል ቢያስተባብሉምየወልቃይትን የማንነት ጥያቄ በተመለከተ በህዝብ የተመረጡ የኮሚቴ አባላት ከክልሉ እውቅና ውጪ በትግራይ ክልል እና በፌድራልየመከላከያ ኃይሎች በስውር ለመያዝ የተደረገውን አፈና የክልሉ ፕሬዝዳንት መቃወማቸው ከፖለቲካዊ ውሣኔዎች ውጪ ለመደረጋቸውና ኃላፊነቱ ተላልፎ ለአቶ ደመቀ መኮንን ለመስጠቱ ምክንያት መሆኑን ማንነታቸው እንዳይገለፅ የጠየቁ የብአዴን አባላት ለዋዜማ ተናግረዋል፡፡

ሰሞኑን በጐንደር በባህርዳርና በሌሎች የክልሉ ከተሞች የተደረገውን የህዝብ ቁጣና ሰልፍ ተከትሎ የፌዴራል መንግሥት የፀጥታኃይሎች በርካታ ሰላማዊ ዜጐችን ከገደሉ በኋላ በፌዴራል መንግሥትና በክልሉ አስተዳዳር መካከል ልዩነት መፈጠሩንና የፌዴራል ሰርአቱታምሷል በሚል የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ገዱ አንዳርጋቸውና ሌሎች የሥራ አስፈፃሚ አካላት ተቃውሟቸውን ለፌዴራል መንግሥትኃላፊዎች መግለፃቸውን ተከትሎ የፕሬዝዳንቱ የፖለቲካዊ ውሣኔዎች ሚና በድርጅቱ ብአዴን ሊ/መንበር ደመቀ መኮነን ስር እንዲሆንይፋዊ ባልሆነ መንገድ መታዘዙን ምንጮቹ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

ጉዳዩን በተመለከተ የተጠየቁት የክልሉ የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ንገሱ ጥላሁን ወሬውን ሃሰት ነው ካሉ በኋላ ሙሉ መረጃከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

ከኢህአዴግ አባል ድርጅቶች አንዱ የሆነው የብሔረ አማራ ዴሞክሲያዊ ንቅናቄ /ብአዴን/ ለማዕላዊ መንግሥቱ መመስረት ከህውሀትእኩል ወይንም በተሻለ መንገድ በትጥቅ ትግሉ ሚና የነበረው ቢሆንም ክልሉ ተጠቃሚ መሆን አልቻለም ሲሉ በድርጅቱ የ35ተኛ ዓመትክብረ በአል ላይ የፖርቲው የሥራ አስፈፃሚ አባልና የጽ/ቤት ኃላፊው አቶ አለምነው መኮንን በይፋ መናገራቸው የሚታወቅ ሲሆን አሁንበክልሉ የተሰማውን ተቃውሞ ተከትሎ ማዕከላዊ መንግሥት በቀጥታ በክልሉ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት የወሰደው እርምጃ ልዩነቱንእንዳሰፋው እየተወራ ነው፡፡

ቀደም ሲል ክልሉን በፕሬዝዳንትነት ሲመሩ የነበሩት አቶ አያሌው ጐበዜ በድንገተኛና ወቅቱን ባልጠበቀ አስቸኳይ ጉባኤ ከሃላፊነታቸውእንዲነሱ መደረጋቸውና ከዚያም በኋላ የሁመራን የድንበር ጉዳይ በተመለከተ ያነሱት ጥያቄ ከማዕከላዊ መንግሥት ጋር ያቃረናቸው ጉዳይመሆኑ ይነገራል፡፡

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ክልሉን በፕሬዘዳንትነት እንዲመሩ ከተሰየሙበት ጊዜ አንስቶ ፖለቲካዊ ውሣኔዎችን መስጠት እንዳልቻሉ ሲነገር ሰንብቷል፡፡ እንደውም ከፕሬዝዳንትነታቸው ለቀዋል ተብሎ ሲነገር የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ነው፡፡

ከዓመት ከመንፈቅ በፊት በተመሣሣይ ሁኔታ ማዕከላዊው መንግሥት በክልሉ ስራዎች ጣልቃ በመግባቱ ምክንያት አቶ ገዱ ከሥልጣንለቀዋል የሚል ዜና መሰማት ጀምሮ ነበር።

ሰሞኑን በጐንደርና በሌሎች በርካታ የክልሉ ከተሞች የተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎችን በተመለከተ የክልሉ መንግሥት የሥራ ኃላፊዎችሰልፉን ህጋዊ ባይሆንም በሰላም የተደረገና የመልካም አስተዳደር እጦት ያመጣው ጥያቄ ነው ብለው መግለጫ ሲሰጡ የማዕከላዊመንግሥት ኃላፊዎች በበኩላቸው ሰልፉን መንግሥትን በኃይል ለመጣል የተደረገና የሻዕቢያ ተላላኪዎች የጠሩት አመፅ ነው ብለው ሲከሱት እንደነበረም የሚታወስ ነው፡፡