ዋዜማ ራዲዮ- አቶ በቀለ ገርባ መራር የእስር ጊዜ አሳልፈው ከተለቀቁ በኋላ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሽግግር ሊኖር የሚችለው “በሰላማዊ ትግል ብቻ ነው” ብለው እንደሚያምኑ አስረግጠው ይከራከሩ ነበር። እኚህ የሰላማዊ ትግል ጠበቃ የፖለቲካ ትግል ስልታቸውና እምነታቸው ዳግም ከመታሰር አላዳናቸውም። ማናቸውንም ተቀናቃኙን (ልጅ ከአዋቂ ሳይለይ) በፍርሀትና በጥርጣሬ የሚመለከተው ገዥው ፓርቲ አቶ በቀለ ገርባን ዳግም ወደ ወህኒ አውርዶ ግፍ እየፈፀመባቸው ይገኛል። የኦሮሚያን ህዝባዊ አመፅ አስተባብራችኋል በሚል አቶ በቀለና ሌሎች የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ አመራሮች ተወንጅለዋል። የአቶ በቀለና ባልደረቦቻቸው የይስሙላ የክስ ሂደት ምን ይመስላል ብለን ሀሳብ እንዲያጋሩን ሁለት እንግዶችን ጋብዘናል። አድምጡት