• ጣልቃ ገብነታችሁን አቁሙልኝ የሚሉ ቅሬታዎች እየተሰሙ ነው

ዋዜማ ራዲዮ-ኢትዮጵያና ሶማሊያ ያላቸው ግንኙነት ውስብስብና ስላም የራቀው ብሎም በሁለት ታላላቅ ጦርነቶች የታጀበ ነበር። ያለፉት አመታት ሶማሊያ በደረሰባት ውስጣዊ ቀውስ ለኢትዮጵያ አደጋ የምትጋብዝ ስጋት መሆን አልተቻላትም። ይልቁንም ኢትዮጵያ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ጣልቃገብነት እንዲኖራት በር የከፈተ ነበር። አሁን አዳዲስ ለዉጦች እያገነገኑ ነው፣ ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ተፅዕኖ ራሷን ለማላቀቅ እየሞከረች ነው። አዳዲሶቹ ለውጦች የኢትዮጵያን ክፍለ አህጉራዊ ጥቅሞች አደጋ ላይ የሚጥሉ፣ ለተቃዋሚ ሀይሎች በር የሚከፍቱ ሊሆኑ ይችላሉ። አሁን ጥያቄው ሶማሊያ በኢትዮጵያ ላይ በሩን ከዘጋች አዲስ አበባ የትኞቹን የማስገደጃ አማራጮች ትጠቀማለች? ሶማሊያስ ኢትዮጵያን “ገለል በይልኝ” ለማለት ምን የምትተማመንበት አማራጭ ይኖራታል? በዚህ ጥንቅር ሰሞነኛውን ከመጋረጃ ጀርባ ያለ እስጥ አገባ ተመልክተነዋል። ዋዜማን አድምጡ አጋሩ -ከታች ዘገባውን በድምፅ

https://youtu.be/jmPID948d9c