Ethiopian Protestors
Ethiopian Protestors

ዛሬ ዛሬ መሰለፍ ቀርቶ ሰልፍ ለማዘጋጀት መጠየቅ በወንጀለኝነት የሚያስፈርጅ ሊሆን ይችላል። ይህን ህገ መንግስቱ የሰጠንንና አለም አቀፍ ጥበቃ ያለውን ሀሳብን በነፃነት የመግለፅና የመሰብሰብ መብት እንዴት ልንነጠቅ በቃን? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው። የሙዚቃ ኮንስርትም ሆነ የፖለቲካ ስብሰባና ሰልፎች የገዥው ፓርቲን መልካም ፈቃድ የሚጠይቁ ችሮታዎች ሆነዋል። ሰልፍ በመደበኛው የፖለቲካ መዋቅር ያልተወከሉና ድምፃቸው በአግባቡ ያልተሰማ የህብረተሰብ ክፍሎች ሀሳባቸውን የሚግልፁበት መድረክ ነው። ፈፅሞ ፈፅሞ ችሮታ አይደለም! እስቲ በጉዳዩ ላይ ለአፍታ ያደረግነውን ውይይት አድምጡት። ዋዜማና የኢትዮዽያ ሰብዓዊ መብቶች ፕሮጀችት በጋራ ያሰናዱት ነው!