20150603_115556በታሪካዊው የዓድዋ ጦርነት አቅራቢያ ኢትዮጵያ የዓለምን ትኩረት የሳበችበት ወቅት ነበር። በጦርነቱም ወቅት     የ Le Temps ጋዜጣ ዘጋቢ በአዲስ አበባ መገኘቱ የድሉን ዜና አውሮፓውያንም በትኩሱ እንዲሰሙት አድርጉዋቸው ነበር። ይህን የአድዋን ጦርነት ዜና የዘገበውም ፈረንሳዊ ጋዜጠኛ ከጋዜጠኝነቱም በላቀ መልኩ የኢትዮጵያ ወዳጅ የነበረና ለኢትዮጵያም ጥናት አስተዋጽዖ ያደረገ ምሑር ነበር። ይህን ሰው ፈረንሳውያኑ ሲጠሩት ሞንዶን ቪዳዬ (Mondon Vidailhet) ይሉታል። እርሱ ግን በአማርኛ ባሳተመው የአፄ ቴዎድሮስ ታሪክ ላይ ራሱን ሞንዶን ዊዳሌ ብሎ ያስተዋውቃል። በዚህ የዋዜማ ሬዲዮ የዚህን ግለሰብ ታሪክ መዝገቡ ኃይሉ አዘጋጅቶ ያቀርበዋል።