በድሬዳዋ ከተማ የሚሰራበት 40-40-20 የተባለው የብሄር የፖለቲካ ኮታ አስከትሎታል የተባለውን ቀውስ ለመቅረፍ የጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ መፍትሄ ለመስጠት ቃል ገብቷል። የጠቅላይ ሚንስትሩ መልዕክተኞች ድሬዳዋ ደርሰው ተመልሰዋል።

Dire Dawa Protest -SM

ዋዜማ ራዲዮ- የጥምቀት በአል የመጨረሻ ቀን ላይ ግጭት ከተቀሰቀሰ በሁዋላ ያለፈውን ሳምንት ድሬዳዋ ሰላሟን አጥታ ሰንብታለች።የከተማዋ መንገዶች ተዘጋግተው ነበር በነበሩ : በሁከቶች ሰዎች ቆስለዋል በርካቶችም ታስረዋል።በጥቅሉም በከተማዋ የነበረው የጸጥታ ችግር የመከላከያ ሰራዊት ተሰማርቶ ጸጥታ የማስከበር ስራ እንዲያከናውን ያስገደደው ነበር።

በዚህች ከተማ የተለያዩ መነሻዎች ተከትሎ ግጭቶች ይነሱ እንጂ የድሬዳዋ ችግር የኢህአዴግ መንግስት ከገባ በሁዋላ በተወሰዱ ርምጃዎች ኢኮኖሚዋ ከመጎዳቱም ባለፈ ከጊዜ በሁዋላ የመጣው 40 40 20 የተባለው አሰራር ነው ስር የሰደደ ችግር ፈጥሯል።ይህንንም የከተማው ነዋሪዎች አፓርታይድ እያሉ ነው የሚጠሩት።ባለፈው ሳምንት በነበረ ተቃውሞም በስፋት አደረጃጀቱ ሲወገዝ ነበር።

ከሳምንት ወዲህ በከተማዋ ችግር ከተፈጠረ በሁዋላ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የቀድሞ ግብርና ሚኒስትር አቶ ተፈራ ደርበውና የቀድሞ የማዕድን ሚኒስትር አቶ መለሰ አለሙ የከተማውን ተወካዮች ለማነጋገር ወደስፍራው አቅንተው ነበር።በዚህ ጊዜም ከከተማው ነዋሪዎች የ40 40 20 ጨምሮ በርካታ የከተማው ችግሮች ተነስቶላቸዋል።የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ተወካዮቹ አቶ ተፈራ ደርበውና አቶ መለሰ አለሙም ተወከዮቹን 40 40 20 የተባለውንና ሌሎች ችግሮችን እንፈታላቹሀለን አንድ ወር ብቻ ጠብቁን የሚል ምላሽን ለተወካዮቹ ሰጥተዋል። አደረጃጀቱን በምን አማራጭ እንደሚፈቱት ባይገልጹም የተሻለ ምላሽ እንደሆነ ግን ታምኖላቸዋል።

በሌላ በኩል ከከተማዋ ወቅታዊ የጸጥታም ሆነ ሌሎች ችግሮች ገር በተያያዘ አሁን ያለው የከንቲባ ኢብራሂም ኡስማን አስተዳደር እንዴት ይሁን የሚለውም ጉዳይም ታይቷል።ከንቲባ ኢብራሂም ከሶማሌ ክልል የቀድሞ አስተዳዳሪ አብዲ መሀመድ ኡመር ጋር ወይንም አብዲ ኢሌይ ጋር ቅርበታቸው የጠበቀ ነው : እሳቸው ሲታሰሩም አጋሮቻቸውን አስጠግተዋቸዋል : የድሬዳዋ የጸጥታ ችግርም መነሻም ይሄው ነው ብሎተ ስለታመነ ከሀላፊነታቸው እንዲነሱ ከፍተኛ ተቃውሞ ተሰምቶባቸዋል።ከሀላፊነቶ ይነሱ ጥያቄ የአቶ ኢብራሂም ምላሽ ግልጽ ባይሆንም በፌዴራል መንግስት በኩል በከተማዋ ችግሮች ላይ ሌሎች ማጣሪያዎች እስኪደረጉ በሀላፊነት እንዲቆዩ የማድረግ ፍላጎት እንዳለ አውቀናል።

ሆኖም አሁን አንጻራዊ ሆኖ የታየው የከተማዋ መረጋጋት እንዲቀጥል በተቃውሞ ወቅት የታፈሱት በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ጉዳን በመልቀቅ መንግስት መፍትሄ ሊሰጥ ይገባል የሚሉ ጥያቄዎችም በስፋት እየተሰሙ ነው። [ዝርዝር የድምፅ ዘገባ ከታች ይመልከቱ]

https://youtu.be/MNYJEcuPkSs