Amhara Protestsዋዜማ ራዲዮ- የዐማራ ብሄረተኝነት ለጋ የፖለቲካ ትርክት ሆኖ የኢትዮጵያን የፖለቲካ መድረክ ተቀላቅሏል። በእርግጥ እንዳሁኑ ሰፊ ህዝብ የተሳተፈባቸው ባይሆኑም ባለፉት ሀያ አምስት አመታት የዐማራ ብሄረተኝነት አጀንዳን ያነሱ ነበሩ። በሌሎች እንደጠላት የሚፈረጀው ዐማራ ከኦሮሞ ብሄረተኞች ጋር በጋራ መቆሙ የሀገሪቱን የወደፊት አቅጣጫ ለመቀየር ትልቅ እርምጃ ነው። እስቲ ውይይቱን አድምጡት።

የኦሮሞ ህዝባዊ አመፅ ሲጀመር ከነበረበት ሲነፃፀር ብዙ ረቀት ተጉዟል፣ የድምፀትና የፖለቲካ ትንተናውም አዲስ መልክ ይዟል። አሁን አሁን ደግሞ ሌላ አዲስ ክስተትን ይዞ ወደ አዲስ ምዕራፍ ተሸጋግሯል። አስቲ አድምጡት

የትግርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን በሀገሪቱ በተከሰተው ህዝባዊ አመፅ ዙሪያ በአመዛኙ “የተለየ አመለካከት” አላቸው፣ ሁኔታው የፈጠረውና ገዥው ፓርቲ በስፋት የሚያሰራጨው ፕሮፓጋንዳ ተጋሩን ከሁለት ያጣ የደረገው መስሏል። ቀላል የማይባል ቁጥር ያለው የብሄሩ ተወላጅ ደግሞ አንድም የፖለቲካ ስልጣን ሌላም የኢኮኖሚ ጥቅም አስሮ ይዞታል ይላሉ ተዋያዮቻችን።

ኢህአዴግ ጥልቅ ተሀድሶ በማድረግ የህዝቡን ጥያቄ እመልሳለሁ እያለ ነው። በተቃራኒው ግን በተቃዋሚዎች ላይ የሀይል እርምጃውን ገፍቶበታል። ድርጅቱ ችግሩን ለመፍታት አቅምም ብቃትም ይጎድለዋል ይላሉ የዋዜማዎቹ ዶ/ር ደረሰ ጌታቸው እና መስፍን ነጋሽ የሚያጋሯችሁን ሀሳብ አድምጡ አጋሩ

ውይይቶቻችንን በዩቱብ (https://www.youtube.com/user/Wazemaradio ) በሳውንድ ክላውድና(https://soundcloud.com/wazema-radio/ )በፌስ ቡክ ማዳመጥ ይቻላል።