Gebeyehu in Cairo with Sisiዋዜማ ራዲዮ- በዓባይ ወንዝ ሳቢያ አንዴ ሲከር ሌላ ጊዜ ሲለዝብ የነበረው የኢትዮጵያና የግብፅ ውዝግብ አሁን አዲስ መልክ ይዟል። በተለይ ያለፉትን ስድስት ወራት ግብፅ ያለ የሌለ አማራጮቿን ተጠቅማ ኢትዮጵያን ለማስገደድ ጥረት አድርጋለች። ይህ ጥረቷ የተወሰነ ውጤት አስገኝቶላታል። ከሰሞኑ ወደ ካይሮ አቅንተው የነበሩት የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ወርቅነህ ገበየሁ የኢትዮጵያን አዲስ የተለሳለሰ አቋም ለግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታ አልሲሲ አቅርበዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ግን ከግብፅ ጋር ከስምምነት ደርሰናል፣ በካይሮ ተጠልለው የነበሩ የተቃዋሚ ሀይሎችንም እንዲባረሩ አድርጊያለሁ እያለ ነው።
የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ሀይሎችን በመደገፍም ይሁን ሌሎች ጫናዎችን በማሳደር ግብፅ አዲስ ዲፕሎማሲያዊ ድል ማግኘቷን የሀገሪቱ የመገናኛ ብዙሀንም አራግበውታል። የህዳሴውን ግድብ ያህል ትልቅ የጂኦፖለቲካል መሳሪያ የያዘችው ኢትዮጵያ ላለፉት ስድስት አመታት የያዘችውን አቋም እንድታለዝብ ያስገደዷት ውስጣዊና ውጪያዊ ምክንያቶች ምንድናቸው? አርጋው አሽኔ ከተለያዩ ምንጮች ያሰባሰበውን መረጃ አክሎ የሚንግረን አለ-ከታች በድምፅ ሙሉ ዘገባውን ይመልከቱ