President Isayas Afeworki
President Isayas Afeworki

ዋዜማ ራዲዮ- ዩናይትድ ስቴትስ በኤርትራ ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ መጣሏን ይፋ አደረገች። ኤርትራ ተጨማሪ ማዕቀብ የተጣለባት ከሰሜን ኮርያ ወታደራዊ የመገናኛ ራዲዮ መግዛቷ ከተደረሰበት በኋላ ነው።ሰሜን ኮርያ ላይ የወታደራዊ ቁሳቁስ ግዥና ሽያጭ ማዕቀብ ከተጣለ አመታት ተቆጥረዋል።

የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ከኤርትራ ባህር ሀይል ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ላለማድረግ የወሰነበትን የማዕቀብ ውሳኔ ሰነድ ይፋ አድርጓል።
በሰነዱ እንደተመለከተው ኤርትራ በቻይና በኩል ከሰሜን ኮሪያ የገዛቻቸው የመገናኛ ራዲዮ መሳሪያዎች ለባህር ሀይሏ አገልግሎት እንዲውሉ የታሰቡ ናቸው።ኤርትራ ከሰሜን ኮርያ ወታደራዊ ቁሳቁስ ስትገዛ ይህ የመጀመሪያዋ አይደለም።
መሳሪያዎቹ የተገዙት በፈረንጅ አቆጣጠር 2016 ሲሆን ጉዳዩ በመንግስታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ባለፈው ወር ይፋ ባደረገው ሰነድ ሰለ ህገ ወጥ ግዥው ተብራርቷል። ኤርትራ በሶማሊያ ያሉ ታጣቂዎችን ትደግፋለች በሚል ማዕቀብ ከተጣለባት ስምንት አመታት ሆኗል። አስመራ ማዕቀቡ ፍርደ ገምድል ነው ስትል ትቃወማለች። ማዕቀቡን የሚያብራራውን ስነድ በማስፈንጠሪያው ያገኙታል-  https://www.gpo.gov/fdsys/pkg/FR-2017-03-30/html/2017-06225.htm