ዋዜማ ራዲዮ- የመንግስታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ አራዘመ።
ማክሰኞ (November 14) ባደረገው ስብሰባው የፀጥታው ምክር ቤት ከስምንት አመት በፊት በኤርትራ ላይ የጣለውን የጦር መሳሪያ ማዕቀብ አራዝሟል። ማዕቀቡ የተጣለው ኤርትራ ለሶማሊያ ሸማቂ ቡድን አልሸባብ ድጋፍ አርጋለች በሚል ነው። ማዕቀቡን የሚቆጣጠረው ኮሚቴ ኤርትራ ባለፈው አንድ አመት ለአልሸባብ ድጋፍ ማድረጓን የሚያረጋግጥ መረጃ አላገኘሁም ቢልም ከ15 የፀጥታው ምክር ቤት አባላት አስራ አንዱ ማዕቀቡ እንዲቀጥል ድምፅ ሲሰጡ ሩሲያ ቻይና ግብፅና ቦሊቪያ ድምፀ ተዐቅቦ አድርገዋል።
ኤርትራ ማዕቀቡ እንዲነሳላት ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ዘመቻ ብታደርግም ውጤት ሳያስገኝ ቀርቷል።
ኤርትራ ከዩናይትድስቴትስ ጋር ያላት የሻከረ ግንኙነት፣ በሀገሯ ያለው መረን የለቀቀ የመብት ጥስትና ከኢትዮጵያ ጋር ያላት መልካም ያልሆነ ግንኙነት ለማዕቀቡ መራዘም አስተዋፃኦ ሊያደግ እንደሚችል ይገመታል።
የምዕራባውያን ሸሪክ የሆነችው ኢትዮጵያማዕቀቡ እንዲራዘም ከፍተኛ ዘመቻ እንደምታደርግ ይታወቃል። በሶማሊያም ላይ ተመሳሳይ ማዕቀብ ተጥሎ የቆየ ሲሆን አሁን በተመሳሳይ ተራዝሟል።