gየታሪክ ተመራማሪ ናቸው፡፡አሁን ለገበያ የቀረበው መጽሐፋቸው እ.ኤ.አ በ2009 በዬል ዩኒቨርስቲ ፕሬስ ታትሞ የነበረ ቢሆንም ለአገር ዉስጥ ገበያ ቀርቦ አያውቅም፡፡ አሁን ግን በተለይ ለኢትዮጵያና ምስራቅ አፍሪካ ገበያ እንዲውል ታስቦ በድጋሚ ታትሟል፡፡ የመጽሐፉ ትኩረት በቅርቡ የአገሪቱ ታሪክ በነበሩት አብዮቶች ላይ ሲሆን The Ethiopian Revolution- War in the Horn of Africa የሚል ርዕስ ተሰጥቶታል፡፡ ከሰሞኑ በኢክሊፕስ ማተሚያ ቤት ታትሞ፣ የአዲስ አበባ መጽሐፍት መደብሮች ለሽያጭ ቀርቧል፡፡

አክሱም የተወለዱት ፕሮፌሰር ገብሩ አስመራ ለአጭር ጊዜ ኖረዋል፡፡ በሥራው ዓለም ረዥም ጊዜያቸውን ያሳለፉት አሜሪካ ሲሆን እዚያም ለ31 ዓመታት ‹‹ሆባርት ኤንድ ዊሊያም ስሚዝ ኮሌጅ›› ዉስጥ በመምህርነት አገልግለዋል፡፡ በወቅቱ ብቸኛው ጥቁር መምህር እንደነበሩም ይነገራል፡፡

የመጀመርያው መጽሐፋቸው Ethiopian Power and Protest; Peasant Revolutions in the Twentieth Century. የሚለው ሲሆን በትግራይ በጎጃምና በባሌ የተካሄዱ አመጾች በሰፊው የተዘገቡበት ነው፡፡ በዚህ ዙርያ እንዲጽፉ ምክንያት የሆናቸው የኢህአፓው መሪ ዶክተር ተስፋዬ ደበሳይ እንደነበረም ያስታውሳሉ፡፡ ይህ መጽሐፍ በኢትዮጵያ የገበሬ አመጽ ዙርያ ከተጻፉ የጥናት ወረቀቶች ሁሉ በመረጃ የበለፀገ እንደሆነ ይነገርለታል፡፡

‹‹The Ethiopian Revolution- War in the Horn of Africa›› የተሰኘው የፕሮፌሰር ገብሩመጽሐፍ 437 ገጾች ሲኖሩት ክብሩ መጻሕፍት መደብር ለአገር ቤት ገበያ በ250 ብር ዋጋ ያከፋፍለዋል፡፡ ፕሮፌሰር ገብሩ በአገር ቤት ሚዲያ የሚታወቁት በአፍቃሬ-ኢህአፓነታቸው ነው።