Bishoftu massacre[ዋዜማ ራዲዮ]

  • 2009 ኢሬቻ በዓል አከባበር ላይ የኦሮሞ ባህላዊ ልብስ የለበሱ የደህንነት ሰዎች ወደ ህዝቡ በዘፈቀደ ሲተኩሱ እንደነበረ እማኞችን ጠቅሶ አለማቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሂውማን ራይትስ ዎች በሪፖረቱ አጋለጠ።

አሜሪካ በበኩሏ ኢትዮጵያ ግልጽና ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ውይይት፣ የመንግሥት አሰራር፤ እንዲሁም የዴሞክራሲ እና የፍትህ ተቋማትን ማጠናከር እንደሚገባት አሳሰበች።

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ሰሞኑን በኦሮሚያሶማሌ ድንበር የተከሰተውን የጎሳ ግጭት አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ውይይት፤ ግልጽ የመንግሥት አሰራር፤ እንዲሁም የዴሞክራሲ እና የፍትህ ተቋማትን ማጠናከር  ለችግሮች ሁሉ ፈጣን እና ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት አሰፈላጊ መሆናቸውን ጠቁሟል፡፡

በኦሮሚያሶማሌ ድንበር በተከሰተው የጎሳ ግጭት ተረብሸናል ያለው ይኸው መግለጫው የኢትዮጵያ መንግሥት ግጭቱን ግልጽ በሆነ አካሄድ እንዲያጣራ እና አጥፊዎችን ተጠያቂ እንዲያደርግ ጠይቋል፡፡

የአሜሪካ መንግስት በነሃሴ 19 ቀን 2009 . ወደ ኢትዮጲያ ለሚደረግ ማንኛውም ጉዞ በድጋሚ ማስጠንቀቂያ ለዜጎቿ ያወጣች መሆኑ ይታወሳል፡፡ ማሰጠንቀቂያው በተለይ በጎንደር፣ ባህርዳር እንዲሁም በአንዳንድ የአማራ እና የኦሮሚያ ክልሎች በሚደረጉ ጉዞዎች ያልታሰበ ህዝባዊ አመፅ እና የዘፈቀደ እስር ሊኖር እንደሚችል ያሰጠነቅቃል።


በሌላ በኩል  መስከርም 9 ቀን 2010 . የወጣው  የሂውማን ራይትስ ዎች ሪፖርት የፖሊስም ሆነ የወታደር ልብስ ያልለበሱ ከህዝቡ ውስጥ ገብተው የህዝቡን አይነት አለባበስ የለበሱ ሰዎች በሽጉጥ በዘፈቀደ ሰዎችን እየተኮሱ እንደገደሉ በእማኞቹ አሰረድቷል። ከደህንነት አባሎቹ  መካከል አንዳንዶቹ የኦሮሞ ባህላዊ ልብስ የለበሱ ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ የወታደርም፣ የፖሊሰም፣ የባህልም ልብስልለበሱ ከታዳሚው ጋር የተቀላቀሉ እና የተመሳሰሉ ነበሩ ሲሉ ቃላቸውን ሰጥተዋል። 

አለማቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሂውማን ራይትስ ዎች በነዳጅ ላይ እሳት 2009 ኢሬቻ በዓል አከባበር የፀጥታ ሃይሎች ምላሽ` በሚል ባወጣው ሪፖርቱ  በልዩ ሁኔታ መንግስት በኢሬቻ 2009 በዓል አከባበር ላይ  የፈፀመውን የሰብዓዊ መብቶች ጥስት በትኩረት ይዳስሳል።  ሪፖርቱ ከጥቅምት 2009 እስክ ነሐሴ 2009 በኢሬቻ በዓል ዕለት እና በዓሉን ተከትሎ በተፈፀሙ ሰብዓዊ መብቶች ጥስት ብቻ ትኩረት አድርጓል።

ቃለመጠይቅ የተደረገላቸው 51 እማኞች ጠቅሶ በተሰራው ይኸው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰትን ያጋለጠው ሪፖርት በአስር የኦሮሚያ ክልላዊ ዞኖች የሚኖሩ 25 ሰዎችን ምስክርነት አካቷል። በበዓሉ ላይ የታደሙ 15 ሰዎች የበዓሉን አከባበር በተመለከተ እና በዓሉን አከባበር ተከትሎ ሰለተከሰተው ብጥብጥ አሰረድተዋል። ሌሎች ጋዜጠኞች መምህራን እና በተለያዩ ሆሰፒታሎች የሚሰሩ የህክምና ባለሙያዎችን እማኝነት ሪፖርቱ አሰገብቷል።

አንድ እማኝ በኢሬቻ በዓል የነበረውን ሁኔታ ለሂውማን ራይትስ ዎች ሲገልፁ፡

ከኔ በቅርብ ርቀት የወታደርም የፖሊስም ልብስ ያለበሱ ሰዎች ወደህዝቡ እየተኮሱ ሰዎች ሲገድሉ አይቻለሁ፡፡አንድ ሰውዬ በቴፒ ዪኒቨርሰቲ መምህር የነበረን ሰው ተኩሶ ሲገድለው አይቻለሁ። መምህሩ በጣም ታዋቂ ነው፣ አውቀዋለሁ። ሲወድቅ አየሁት። ልረዳው አልቻልኩም ምክንያቱም እኔም ህይወቴን ለማዳን እየሮጥኩ ነበር፡፡ሌሎችም ሰዎች በጥይት ተመተው ሲወድቁ አይቻለሁ። ሰውነታቸው በጥይት ተመቶ ነው የወደቁት

2009 የኢሬቻ በዓል እንዳትሳተፉ ተብለው በመንግስት የድህንነት አባላቶች እና በኦሆዴድ ካደሬዎች ማሰጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው እንድነበር የተናገሩ እማኞች ማሰጠንቀቂያውን ችላ በማለት በዓሉ ላይ እንደተሳተፉ ገልፀው ከበዓሉ በኃላ ወደ መንደራቸው ሲመለሱ ያለምንም የፍርድቤት ትዕዛዝ እንደታሰሩ እና በእስር ወቅትም ከባድ ድብደባ እንደደረሰባቸው ሪፖርቱ ጠቅሷል፡፡ እስር ይገጥመናል በለው በፍራቻ ወደ ቤታቸው እንዲሁም መንደራቸው ያልተመለሱ ደግሞ ቤተሰቦቻቸው በእነርሱ ምትክ እንደታሰሩባቸው ተናግረዋል።

ለበርካታ አመታት የኢሬቻ በዓል ላይ ተሳትፎ እንድነበራቸው የተናገሩ ግልስብ እንዲህ ብልው እማኝነታቸውን ሰጥተዋል፡

ሌላ ጊዜ በኢሬቻ በዓል የከተማው ፖሊሰ ነበር ኃላፊነት የሚወስዱት።እናወቃቸዋልን፣ ያውቁናል። የምናወራውን ያወራሉ። በዓሉ ለኛ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ያውቃሉ። ቦታውንም ገደል ጉድጓዱንም በደንብ ያወቁታል። በዚህ አመት የፌደራል ፖሊሶች ነበሩ። የማላውቀውን ቋንቋ የሚናገሩ፤ በከባድ የታጠቁ። የኦሮሚያ ፖሊስ እንድዚህ አይታጠቅም። በዓሉን የወታደራዊ ተልእኮ ነው ያሰመሰሉት፡፡

መንግስት 55 ሰዎች በመረጋገጥ እና ጉድጓድ ውስጥ በመግባት ሞተዋል ያለ ቢሆንም ሶስት ሰማቸው ቢጠቀስ ለደህንነታችን ያሰጋናል ያሉ  የቢሾፍቱ ሆሰፒታል ሰራተኞች፣ የመንግስት የደህንነት ሃይሎች ሆሰፒታል ድርስ በመምጣት ጋዜጠኞች እና ሌላ ማንም ቢጠይቃችሁ `የሞቱ ሰዎች ቁጠር 55 ነው፤ የሞታቸው ምክንያት ደግሞ ተረጋግጠው ነው` ብላችሁ መልሱ ሰለመባላቸው ለሂውማን ራይትስ ዎች  አጋልጠዋል።

ነዋሪነቱ ሻሸመኔ የሆነ 21 አመት ወጣት 2009 ኢሬቻን አሰምልክቶ ለሂወማን ራይትስ ዎች ሲናገር

በበዓሉ ቦታ ሰደርስ በፊት የማውቀው ኢሬቻ በዓል እና የማየው ኢሬቻ አንድ አልሆንብኝም። የወታደር መኪናዎች ሁሉም ቦታዎች ላይ ነበሩ። በዓሉ ወደሚከበርበት ቦታ ስጠጋ የኦሮሞ የበዓል ልብስ የለበሱ የደህንነት ሰራተኞች ሰዎችን እያሰሩ ሲወሰዱ አየሁ። ተራ ልብስ የለበሱ ደህንነቶችም ሰዎችን ሲያሰሩ አይቻለሁ። የኢሬቻ ጠቅላላ መንፈስ በቦታው አልነበረም። የሆነ የፖለቲካ ሰብሰባ ነበር የሚመስለው እንጂ ባህላዊ ወይንም ሃይማኖታዊ በዓል አይመሰልም ነበር።

ዘንድሮ መስከረም 21 ቀን 2010 የሚከበረው ኢሬቻ በዓል  ያለምንም ጣልቃገብነት በሰላም እንዲከበር እንዲሁም የመንግስት ፀጥታ ሃይሎች ማንኛውንም አላግባብ ያልሆን ሃይል ከመጠቀም እንዲቆጠቡ አለማቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ሂውማን ራይትስ ዎች ጠይቆ በዓሉ በሰላም እንዲከበር መንግስት አሰፈላጊውን ሁሉ ትብብር እንዲሁም ዝግጅት በማድረግ ግርግር እና ብጥብጥ እንዳይፈጠር ከህዝብ ጋር አላግባብ መፋጠጥ ውስጥ እንዳይገባም አሳስቧል።

ወደ በዓል አከባበሩ  መውጫና መግቢያ በፀጥታ ሃይሎች እንዳይዘጉ የኢሬቻ በዓል አከባበር ካውንስል እንዲያሰተባብር ወደ ሓይቁ የሚወሰዱ ገደላማ ቦታዎች እንዲከለሉ( እንዲታጠሩ) አሊያም አደጋ በማያደርስ መንገድ በምልክት እንዲገልፁ ድርጅቱ ተማፅኗል።

2009 ኢሬቻ በዓል ላይ የሞቱትንም ሰዎች አስምልክቶ ሂውማን ራይትስ ዎች መንግስት የፀጥታ ሃይሎች ሰለተጠቀሙት አግባብ ያልሆነ ሃይል ገለልተኛ የሆን አጣሪ እንዲያቋቁም፣ ቤተሰቦች ሰለጠፉባቸው፣ ሰለሞቱባቸው የቤተሰቦቻቸው አባላት አግባብ የሆነ መረጃ እንዲሰጣቸው እንዲሁም በዓሉን ለማክበር በቦታወ ሰለተገኙ ብቻ ወይም በበዓሉ ላይ በነፃነት የመናገር መብታቸውን ሰለተጠቀሙ በቻ የተከሰሱ እና የታሰሩ ሰዎች እንዲፈቱና ክሳቸውም እንዲነሳ ጠይቋል።