10603293_646024532185250_8094873702801659572_n

የለውጥ ዘመን ላይ መኖር ለጸሐፍያን የማይገኝ እድል ኾኖ ይቆጠራል። ምክንያቱም እንዲህ ያለ ወቅት እጅግ ብዙ የሥነጽሑፍ ግብአት የተከማቸበት አጋጣሚም ስለሚኾን ነው። የግርማ ተስፋው “ሰልፍ ሜዳ” ም ይህን ከመሰለው ዘመን የተወሰደ ያለፈ ታሪካችን ክፋይ ነው።

በልቦለድ ጸሐፍያን ዘንድ ብዙም ያልተባለለትን የ1983 ቱን ግርግር ዋነኛ ዓውዱ ያደረገው ይህ መጽሐፍ፤ ብዙ ሊባልበት የሚችል ቢኾንም ከገጸ ባህርያቱ መካከል ጉልህ ሥፍራን የያዘውን ንጉሤ ጥጋቡን በማንሳት በዚህ የምእራፍ አንድ ዝግጅታችን ሰልፍ ሜዳን ለማሰስ እንሞክራለን። ከታች ያድምጡት