President-Isaias-Afewerki-Eritreaዋዜማ ራዲዮ- ኤርትራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ወደ አዲስ አበባ ለመላክ እየተዘጋጀች መሆኑን ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ተናገሩ።
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በየዓመቱ በሚከበረው የሰማዕታት መታሰቢያ ላይ በቀጥታ የቴሌቭዥን ስርጭት እንደተናገሩት በድንበር ጉዳይ ላይ የሚነጋገር የልዑካን ቡድን ወደ አዲስ አበባ ለመላክ ሀሳብ አላቸው። ተጨማሪ ዝርዝር አልሰጡም። በጃፓን የኤርትራ አምባሳደር እስጢፋኖስ አፈወርቂም ይህንኑ መረጃ በትዊተር ገፃቸው አስነብበዋል።

በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል በሶስተኛ ወገን ምስጢራዊ ውይይት ላለፉት አራት ሳምንታት ሲካሄድ ቆይቷል። ሁለቱን ሀገራት ለማቀራረብ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና ሳዑዲ አረቢያ ጥረት ሲያደርጉ ነበር። የአውሮፓ ህብረትም ኤርትራን በማግባባት ጥረት ሲያደርግ ሰንብቷል።
የኤርትራው ፕሬዝዳንንት ኢሳያስ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ያላቸውን ግንኙነትም ያለቅድመ ሁኔታ እንደሚያሻሽሉ ተናግረዋል።

ስለዲፕሎማቲክ ጥረቱ ዝርዝር እዚህ ያንብቡ-https://goo.gl/4D9vyR