ሀገሪቱ አንድ ከሚያደርጓት እውነታዎች ይልቅ ልዩነትና መቃቃር እያየለ የመምጣቱ ጉዳይ የሚያሳስባቸው ኢትዮዽያውያን ብዙ ናቸው። ሁሉን በአንድ የሚሰባስበው “ኢትዮዽያዊነት” እንደ ጨቋኝ ሀሳብ መታየት ከጀመረም ስነባብቷል። “ኢትዮዽያዊነት” ሌሎች ዘውጌ ብሄረተኞችን የማፈኛ መሳሪያ መሆኑንም የሚያስረዱና የሚከራከሩ አሉ።አማራነትና ኢትዮዽያዊነት ምንና ምን ናቸው? የዕለቱ ውይይታችን በዚህ ላይ ያተኩራል። አድምጡ ሀሳባችሁን ስደዱልን ። wazemaradio@gmail.com
የመጀመሪያውን ክፍል ውይይት እዚህ ያድምጡ- http://wazemaradio.com/?p=1972
የአንድዮሽ ዉይይት/ወሬ
ብዙ ብዙ ብላችሁዋል፡፡ ነገር ግን ሁሉም በተቃራኒ ሀሳብ ያልተፈተነ የራሳችሁ ምኞትና አመለካካት ብቻ ናቸዉ፡፡ እስቲ ካነሳችሁት ሀሳቦች ፍጹም ከእዉነት የራቀ አንድ ምሳሌ ልጥቀስ፡፡ (አዉቆ የተኛን ……… ነገር ይሆናልና ማብራርያ ግን አልሰጥም ፡፡)
1. የኃይለሥላሴ መንግሥት አማራንና ኦሮሞን በእኩልነት ጨቁኖዋል፡፡ ቂቂቂቂቂቂቂ
2. የብሔር ማንነት እንዲከበር የጠየቁት፣ የታገሉትና አሁን ያለዉን የብሔር ፌዴራሊዚም ያመጡት እንድ ቡድን (ሕወሓት) ብቻ እንደሆኑ አድርጋችሁ ማቅረባችሁ ደግሞ በኢትዮጵያ የተለመደዉን የታሪክ ቅጥፈት መድገማችሁን ያሳያል፡፡
What a great discourse and insight.
There was and there is and there will be Ethiopia Ethiopians and Ethiopianism forever.
Commentየመከራዉን ኑሮ እየኖርን ያለን እኛ አማራወች ነን
Comment የመከራዉን ኑሮ የምንኖረዉ እኛ አማራወች ነን
ጅማሬያችሁ ጥሩ ነው፤ ቀጥሉበት በተጨማሪም በሀገራችን ማየት የናፈቀንን የሰለጠነ ውይይት በጉዳዩ ላይ አቋማቸውን በሶሻል ድረገፅዎች ላይ እያንፀባርቁ ያሉ አክቲቪስቶችን ተሳታፊ በማድርግ አሰሙን፡፡ ይህን ስል ከጉዳዩ ስስነት አንፃር በጋበዝም የማይመጣ እንደሚኖር አምናሉሁ ግን ቢሆንም ጋብዙ መጋበዛችሁንም አሳውቁን ፡፡
እኔ በዚህ ጉዳይ ላይ ቢያንስ ከ3ቱም ጎራዎች (ከኢትዮጲያውነት አቀንቓኞች ለምሳሌ ታምራት ነገራ፤ ከኦሮሞ አከተቪስቶች ለምሳሌ ጃዋር፤ ከኢሃዲግ ደጋፊዎች፤ ጉዳዩ ላይ እውቀቱ እና ፍቃደኛነቱ ያለው አንድ ካድሬ)ተወካይ ይዛችሁ ብታስደምጡን እመርጣለሁ፡፡
ጥያቄ እና መልስ ግን ሪኣክተቭ በሆነ መንገድ ሊበራሩ እና ሊተቹ የሚገባቸውን ሃሳቦች በአንድ ወገን ምላሽ እንዲታለፉ ያደርጋል፤ ደግሞስ ውይይት እንጂ አስፈላጊው በዚህ ጉዳይ ማን ጠያቂ ማን መላሽ ብቻ ይሆናል፡፡ ያንድ ወገን ሃሳብ ብቻ ለመተንተን ኢሳት እና አቢሲ ይበቃሉ ፡)
ዛሬ የተከራከርንበት ከነገ ከጦርነት ያተረፈናል፡፡
ሰለሞን

መልካም ቀን!
ሰለሞን
ያቀረባችሁት የታሪክ ትንተና ደስ ይላል።
“ኢትዮጵያዊ ብሔረተኝነት” እንዲህ ባሉ ውሃ ውሃ በሚሉ መከራከሪያዎች ላይ መቆሙን ማወቅ ያሳቅቃል፤ ያስቃልም።